Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 7:86 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

86 ዕጣን የሞላባቸው ዐሥራ ሁለቱ የወርቅ ጭልፋዎችም እያንዳንዳቸው በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ሰቅል መዘኑ፤ በአጠቃላይ የወርቅ ጭልፋዎቹ ክብደት አንድ መቶ ሃያ ሰቅል ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

86 ዕጣንም የተሞሉት ዐሥራ ሁለቱ የወርቅ ሙዳዮች፥ እያንዳንዳቸው በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ሰቅል ነበሩ፤ የሙዳዮቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሀያ ሰቅል ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

86 ዐሥራ ሁለቱ ከወርቅ የተሠሩት የዕጣን ማስቀመጫዎች በመቅደሱ ሚዛን መሠረት እያንዳንዳቸው ዐሥር ሰቅል የሚመዝኑ ሲሆኑ በጠቅላላው አንድ መቶ ኻያ ሰቅል ይመዝኑ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

86 ዕጣ​ንም የተ​ሞሉ ዐሥራ ሁለት የወ​ርቅ ጭል​ፋ​ዎች፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ በመ​ቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ዐሥር ሰቅል ነበረ፤ የጭ​ል​ፋ​ዎቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሃያ ሰቅል ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

86 ዕጣንም የተሞሉ አሥራ ሁለቱ የወርቅ ጭልፋዎች፥ እያንዳንዱ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን አሥር አሥር ሰቅል ነበረ፤ የጭልፋዎቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሀያ ሰቅል ነበረ።

参见章节 复制




ዘኍል 7:86
6 交叉引用  

ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ጽዋዎችን፣ የመብራት መኰስተሪያዎችን፣ ለመርጫ የሚሆኑ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፣ ጭልፋዎችን፣ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎችን፣ ለውስጠኛው ክፍል ለቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ በሮች የሚሆኑ የወርቅ ማጠፊያዎችን።


ለመጠጥ ቍርባን መፍሰሻ ይሆኑም ዘንድ ዝርግ ሳሕኖችንና ወጭቶችን፣ እንዲሁም ማንቈርቈሪያዎቹንና ጐድጓዳ ሳሕኖቹን ከንጹሕ ወርቅ ሥራቸው።


ማንም ወደ ተቈጠሩት ዘንድ የሚያልፍ ሃያ አቦሊ በሚመዝን በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ግማሽ ሰቅል መስጠት አለበት፤ ይህ ግማሽ ሰቅል ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።


እያንዳንዱ የብር ሳሕን መቶ ሠላሳ ሰቅል፣ እያንዳንዱም ጐድጓዳ ሳሕን ሰባ ሰቅል፣ በአጠቃላይም የብር ሳሕኖቹ ክብደት በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ሁለት ሺሕ አራት መቶ ሰቅል ይመዝን ነበር።


ለሚቃጠል መሥዋዕት የቀረቡት እንስሳት የእህል ቍርባናቸውን ጨምሮ ድምራቸው፦ ዐሥራ ሁለት ወይፈን፣ ዐሥራ ሁለት አውራ በግ፣ ዐሥራ ሁለት አንድ ዓመት የሆናቸው ተባዕት የበግ ጠቦቶች ሆነ፤ እንዲሁም ለኀጢአት መሥዋዕት የቀረቡ ዐሥራ ሁለት ተባዕት ፍየሎች ነበሩ።


ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋራ አዩ፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት። ሣጥኖቻቸውን ከፍተው ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤም አቀረቡለት።


跟着我们:

广告


广告