ዘኍል 5:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ከሌላ ሰው ጋራ ብትተኛ፣ ይህም እጅ ከፍንጅ ባለመያዟ ምክንያት ይህ ከባሏ ቢደበቅ፣ የሚመሰክርባት ሰው ባይኖርና መርከሷም ባይገለጥ፣ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ከሌላም ሰው ጋር ብትተኛ፥ ከባልዋም ዐይን ቢሸሸግ፥ እርሷም ተሰውራ ብትረክስ፥ ምስክርም ባይኖርባት፥ በምንዝርም ባትገኝ፥ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ባልዋም ሳያውቅ ከሌላ ወንድ ጋር በመተኛት ምንም ሳይታወቅባት ራስዋን አርክሳ ይሆናል፤ እጅ ከፍንጅም ባለመያዝዋ በእርስዋ ላይ መስካሪ አይኖርም፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ሌላም ሰው ከእርስዋ ጋር ቢተኛ፥ ብታመነዝር፥ ከባልዋም ዐይን ቢሸሸግ፥ እርስዋም ተሰውራ ብትረክስ፥ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ከሌላም ሰው ጋር ብትተኛ፥ ከባልዋም ዓይን ቢሸሸግ፥ እርስዋም ተሰውራ ብትረክስ፥ ምስክርም ባይኖርባት፥ በምንዝርም ባትገኝ፥ 参见章节 |