Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 4:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እንግዲህ የሜራሪያውያን ጐሣዎች በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር ሥር ሆነው በመገናኛው ድንኳን ሲሠሩ አገልግሎታቸው ይህ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር ቁጥጥር ሥር ሆነው በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ባለው አገልግሎታቸው ሁሉ የሜራሪ ልጆች ወገኖች አገልግሎት ይህ ነው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር ተቈጣጣሪነት የሚካሄደው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሜራሪ ልጆች ቤተሰብ አገልግሎት ይህ ነው።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ ባለው ሥራ​ቸው ሁሉ የሜ​ራሪ ልጆች ወገ​ኖች አገ​ል​ግ​ሎት ይህ ነው፤ እነ​ር​ሱም ከካ​ህኑ ከአ​ሮን ልጅ ከኢ​ታ​ምር እጅ በታች ይሆ​ናሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 የሜራሪ ልጆች ወገኖች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከኢታምር እጅ በታች በየአገልግሎታቸው ሁሉ ይህ ነው።

参见章节 复制




ዘኍል 4:33
7 交叉引用  

ለማደሪያው ድንኳን፣ ይኸውም ለምስክሩ ድንኳን ሙሴ ባዘዘው፣ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር መሪነት ሌዋውያኑ በጻፉት መሠረት የዕቃዎቹ ቍጥር ይህ ነው።


ሰውም በአባቱ ቤት ከወንድሞቹ አንዱን ይዞ፣ “አንተ ልብስ ስላለህ መሪ ሁነን፤ ይህንም የፍርስራሽ ክምር ግዛ!” ይለዋል።


እንግዲህ የጌርሶናውያን ጐሣዎች በመገናኛው ድንኳን የሚኖራቸው አገልግሎት ይህ ነው፤ ተግባራቸውም በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አመራር ሥር ይሆናል።


እንደዚሁም በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን ምሰሶዎች ከነመቆሚያ እግሮቻቸው፣ ካስማዎችን፣ ገመዶችን፣ ከእነዚሁ ጋራ ያሉትን ዕቃዎች ሁሉና ማንኛውም ለአገልግሎቱ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ይሸከማሉ። እያንዳንዱ ሰው የሚሸከመውን ዕቃ ለይታችሁ በስሙ መድቡለት።


ሙሴ፣ አሮንና የማኅበረ ሰቡ አለቆች ቀዓታውያንን በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው ቈጠሯቸው።


ለሜራሪያውያንም ለአገልግሎታቸው በሚያስፈልጋቸው መጠን አራት ሠረገሎችና ስምንት በሬዎች ሰጠ። እንግዲህ እነዚህ ሁሉ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር ኀላፊነት የሚመሩ ነበሩ።


ኢያሱም ካህናቱን፣ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክማችሁ ሕዝቡን ቀድማችሁ ሂዱ” አላቸው፤ እነርሱም ታቦቱን ተሸክመው ሕዝቡን ቀድመው ሄዱ።


跟着我们:

广告


广告