ዘኍል 4:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም27 የጌርሶናውያን አገልግሎት ሁሉ፣ ሸክምም ሆነ ሌላ ሥራ አሮንና ልጆቹ በሚሰጡት አመራር መሠረት ይሆናል። የሚሸከሙትን ሁሉ በኀላፊነት ታስረክቧቸዋላችሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 የጌድሶናውያን አገልግሎት ሁሉ፥ ሸክማቸውም ሁሉ፥ ሥራቸውም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ ትእዛዝ ይሁን፤ በየአገልግሎታቸውም የሚደርስባቸውን ሸክም ሁሉ ለእያንዳንዳቸው ትደለድላላችሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 በሚሸከሙአቸው ነገሮችና በሚሠሩአቸው ሥራዎች የጌርሾንን ልጆች አገልግሎት አሮንና ልጆቹ ይቈጣጠሩአቸዋል፤ መሸከም ያለባቸውንም ነገሮች ሁሉ ትመድብላቸዋለህ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 የጌድሶን ልጆች አገልግሎት ሁሉ፥ በተራቸውም ሁሉ፥ በሥራቸውም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ ትእዛዝ ይሁን፤ በስማቸውና በተራቸውም ትቈጥራቸዋለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 የጌድሶናውያን አገልግሎት ሁሉ፥ ሸክማቸውም ሁሉ፥ ሥራቸውም ሁሉ በአሮንና በልጆቹ ትእዛዝ ይሁን፤ የሚደርስባቸውንም ሸክም ሁሉ ትነግሩአቸዋላችሁ። 参见章节 |