Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 36:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የእስራኤላውያን ዓመተ ኢዮቤልዩ በሚመጣበት ጊዜ የእነርሱ ድርሻ ወደ ባሎቻቸው ነገድ ይጨመራል፤ ይህ ከሆነም ድርሻቸው ከአባቶቻችን ነገድ ርስት ላይ ይወሰዳል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ለእስራኤልም ልጆች ኢዮቤልዩ በመጣ ጊዜ ርስታቸው እነርሱ ወደ አሉበት ነገድ ርስት ይጨመራል፤ ርስታቸውም ከአባቶቻችን ነገድ ርስት ይወሰዳል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ንብረት በሚመለስበት ዓመት የተሸጠ ንብረት ሁሉ ለባለቤቱ በሚመለስበት ጊዜ የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች ርስት አግብተው ወደ ሄዱበት ነገድ ለዘለቄታው ተጨማሪ ሆኖ ይተላለፋል፤ ይህም በእኛ ነገድ ይዞታ ላይ ጒድለትን ያስከትላል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኢዮ​ቤ​ልዩ በሆነ ጊዜ ርስ​ታ​ቸው ሴቶቹ ወደ አገ​ቡ​በት ወደ ሌላ ነገድ ርስት ይጨ​መ​ራል፤ እነሆ፥ ርስ​ታ​ቸው ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ነገድ ርስት ይጐ​ድ​ላል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ለእስራኤልም ልጆች ኢዮቤልዩ በመጣ ጊዜ ርስታቸው ለሚሆኑበት ነገድ ርስት ይጨመራል፤ እነዚህም ርስታቸው ከአባቶቻችን ነገድ ርስት የጐድላል።

参见章节 复制




ዘኍል 36:4
7 交叉引用  

የተወደደችውንም የእግዚአብሔርን ዓመት፣ የአምላካችንንም የበቀል ቀን እንዳውጅ፣ የሚያለቅሱትን ሁሉ እንዳጽናና ልኮኛል፤


“ ‘መሬት ለዘለቄታ አይሸጥ፤ ምክንያቱም ምድሪቱ የእኔ ናት፤ እናንተም መጻተኞችና እንግዶች ናችሁ።


“ ‘ሰባት የሰንበት ዓመታት ማለትም ሰባት ጊዜ ሰባት ዓመታትን ቍጠር፤ ሰባቱ የሰንበት ዓመታትም አርባ ዘጠኝ ዓመታት ይሆናሉ።


ከሌሎች የእስራኤል ነገዶች ባል ቢያገቡ ድርሻቸው ከእኛ የዘር ርስት ላይ ተወስዶ የሚያገቧቸው ሰዎች ላሉበት ነገድ ይተላለፋል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ በዕጣ ከተደለደለልን ርስት ላይ ከፊሉ ሊቀነስብን ነው።


ከዚህ በኋላ ሙሴ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “የዮሴፍ ነገድ የተናገረው ትክክል ነው፤


跟着我们:

广告


广告