Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 35:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እነዚህም ስድስት ከተሞች ሳያስበው ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው እንዲሸሽባቸው ለእስራኤላውያን፣ ለመጻተኞችና በመካከላቸው ለሚኖር ለማንኛውም ሕዝብ የመማፀኛ ቦታዎች ይሆናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በስሕተት ነፍስ የገደለ ሁሉ እንዲሸሽበት እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸው ለሚቀመጡ እንግዶችና መጻተኞች መማፀኛ ይሆናሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እነርሱም ለእስራኤላውያንና ለጊዜውም ሆነ ለዘለቄታው በእስራኤል ለሚኖሩ መጻተኞች የመማጠኛ ከተሞች ይሆናሉ፤ ባለማወቅ ተሳስቶ ሰው የሚገድል ማንኛውም ግለሰብ ከእነርሱ ወደ አንዱ አምልጦ መጠጋት ይችላል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ባለ​ማ​ወቅ ነፍስ የገ​ደለ ሁሉ ይሸ​ሽ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ዚህ ስድ​ስት ከተ​ሞች ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ቀ​መጡ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች መማ​ፀኛ ይሆ​ናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በስሕተት ነፍስ የገደለ ይሸሽበት ዘንድ እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸው ለሚቀመጡ እንግዶችና መጻተኞች መማፀኛ ይሆናሉ።

参见章节 复制




ዘኍል 35:15
8 交叉引用  

በመሬት ላይ የፈሰሰ ውሃ እንደማይታፈስ ሁሉ፣ እኛም እንደዚሁ እንሞታለን፤ እግዚአብሔር ግን ከአገር የተሰደደ ሰው ከርሱ እንደ ራቀ በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።


ይህም ሕግ በዜጋውም ሆነ በመካከላችሁ በሚኖሩት መጻተኞች ላይ እኩል ተፈጻሚነት ይኖረዋል።”


ለመጻተኛው ሆነ ለአገር ተወላጅ አንድ ዐይነት ሕግ ይኑራችሁ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።’ ”


“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፤ ‘ማንም ሰው ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸውም አንዱን ተላልፎ ቢገኝ፤


ለእናንተም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖር መጻተኛ ይኸው ሕግና ሥርዐት እኩል ተፈጻሚነት ይኖረዋል።’ ”


ሳያስበው ሰው የገደለ ሰው ሸሽቶ የሚጠጋባቸው ከተሞች እንዲሆኑ መማፀኛ ከተሞችን ምረጡ።


እግዚአብሔር የአይሁድ አምላክ ብቻ ነውን? የአሕዛብስ አምላክ አይደለምን? አዎን፤ የአሕዛብም አምላክ ነው፤


በአይሁድና በግሪክ፣ በባሪያና በነጻ ሰው፣ በወንድና በሴት መካከል ልዩነት የለም፤ ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ናችሁ።


跟着我们:

广告


广告