Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 29:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ማስተስረያ እንዲሆንም ለኀጢአት መሥዋዕት ከሚቀርበው እንዲሁም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ በመደበኛነት ቀርቦ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንዲሁም ከሚያስተሰርየው ከኃጢአት መሥዋዕት፥ ዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፥ ከመጠጥ ቁርባናቸውም ሌላ ለኃጢአት መሥዋዕት ደግሞ አንድ አውራ ፍየል አቅርቡ።።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለ ኃጢአት ስርየትም የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል ታቀርባላችሁ፤ እርሱም ለሕዝቡ የማስተስረይ ሥርዓት በተፈጸመበት ጊዜ ከሚቀርበው ተባዕት ፍየል እንዲሁም ከእህል ቊርባንና ከመጠጥ መባ፥ በየቀኑ ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ተጨማሪ ሆኖ የሚቀርብ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል አቅ​ርቡ። ከሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ር​የው ከኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ በዘ​ወ​ት​ርም ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም ሌላ አቅ​ር​ቡት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ለኃጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል አቅርቡ። ከሚያስተሰርየው ከኃጢአት መሥዋዕት፥ በዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጥ ቍርባናቸውም ሌላ አቅርቡት።

参见章节 复制




ዘኍል 29:11
10 交叉引用  

መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፤ እግዚአብሔር ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት ቢያደርገውም እንኳ፣ ዘሩን ያያል፤ ዕድሜውም ይረዝማል፤ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።


“ወደ ተቀደሰው ስፍራ በሚገባበት ጊዜ፣ አሮን እንዲህ ያድርግ፤ ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይዞ ይምጣ፤


ከእስራኤል ማኅበረ ሰብ ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለት ተባዕት ፍየሎች፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ይውሰድ።


በዕጣ ለእግዚአብሔር የደረሰውንም ፍየል አምጥቶ ለኀጢአት መሥዋዕት በማድረግ ይሠዋ።


ከሰባቱ የበግ ጠቦቶችም ከእያንዳንዳቸው ጋራ በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት አዘጋጁ።


እነዚህ እንግዲህ በተደነገገው መሠረት ከእህል ቍርባናቸውና ከመጠጥ ቍርባናቸው ጋራ በየዕለቱና በየወሩ ከሚቀርቡት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሌላ ተጨማሪ ሆነው፣ ለእግዚአብሔር ሽታቸው ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ናቸው።


እርሱም እንደ ሌሎቹ ሊቃነ ካህናት መጀመሪያ ስለ ራሱ ኀጢአት፣ ከዚያም ስለ ሕዝቡ ኀጢአት በየቀኑ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ራሱን በሰጠ ጊዜ፣ ስለ ኀጢአታቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት አቅርቧልና።


跟着我们:

广告


广告