ዘኍል 27:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የአፌር ልጅ፣ የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ጐሣዎች ነበሩ፤ ስማቸውም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላል። እነርሱም፣ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 የሰለጰዓድም ሴቶች ልጆች ቀረቡ፤ እርሱም ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ወገኖች፥ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጅ የኦፌር ልጅ ነበር፤ የእነዚህም ሴቶች ልጆች ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 የሔፌር፥ የገለዓድ፥ የማኪር፥ የምናሴ፥ የዮሴፍ ልጅ የሆነው ጸሎፍሐድ፥ ማሕላ፥ ኖዓ፥ ሖግላ፥ ሚልካ እና ቲርጻ ተብለው የሚጠሩ ሴቶች ልጆች ነበሩት። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ወገን ፥ የምናሴ ልጅ፥ የማኪር ልጅ፥ የገለአድ ልጅ፥ የኦፌር ልጅ፥ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች መጡ፤ የእነዚህም ሴቶች ልጆች ስሞች መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ወገኖች፥ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጅ የኦፌር ልጅ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች ቀረቡ፤ የእነዚህም ሴቶች ልጆች ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። 参见章节 |