Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 26:55 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

55 የመሬት ድልድሉም በዕጣ ይሁን፤ እያንዳንዱ የሚወርሰውም በየነገድ አባቶቹ ስም ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

55 ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፋፈላለች፤ እንደ አባቶቻቸው ነገድ ስም ይወርሳሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

55 ሆኖም ክፍፍሉ የሚደረገው በዕጣ ነው፤ ዕጣውም የሚጣለው በየነገዱ መሠረት ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

55 ነገር ግን ምድ​ሪቱ በየ​ስ​ማ​ቸው በዕጣ ትከ​ፋ​ፈ​ላ​ለች፤ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ነገድ ይወ​ር​ሳሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

55 ነገር ግን ምድሪቱ በዕጣ ትከፈላለች፤ እንደ አባቶቻቸው ነገድ ስም ይወርሳሉ።

参见章节 复制




ዘኍል 26:55
21 交叉引用  

ዕጣ በጕያ ውስጥ ይጣላል፤ ውሳኔው በሙሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።


ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።


ለራሳችሁ፣ በመካከላችሁ ለሚኖሩት ልጆች ላሏቸው መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ መድቡ፤ እነርሱንም እንደ እስራኤል ተወላጆች ቍጠሯቸው፤ እንደ እናንተ ከእስራኤል ነገዶች ርስት ይመደብላቸው።


እያንዳንዱም ርስት በትልልቆቹና በትንንሾቹ ነገዶች መካከል በዕጣ ይደለደላል።”


ምድሪቱንም በየጐሣዎቻችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ከፍ ያለ ቍጥር ላለው ሰፋ ያለውን፣ ዝቅተኛ ቍጥር ላለው ደግሞ አነስተኛውን ስጡ፤ ምንም ይሁን ምን በዕጣ የወጣላቸው፣ የየራሳቸው ርስት ይሆናል። አከፋፈሉም በየአባቶቻችሁ ነገዶች አንጻር ይሁን።


ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፤ “ይህችን ምድር ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ደልድሉ፤ እግዚአብሔርም ለዘጠኙና ለግማሹ ነገድ እንድትሰጥ አዝዟል፤


እንዲህም አሉ፤ “ምድሪቱን በዕጣ ከፋፍለህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርገህ እንድትሰጣቸው እግዚአብሔር አንተን ጌታዬን ባዘዘ ጊዜ የወንድማችንን የሰለጰዓድን ድርሻ ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አዝዞሃል።


ከዚያም ዕጣ ጣሉላቸው፤ ዕጣውም ለማትያስ ወጣ፤ እርሱም ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋራ ተቈጠረ።


በቅዱሳን ርስት በብርሃን ተካፋዮች ለመሆን ያበቃንን አብን እንድታመሰግኑ ነው።


ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ምድሪቱን በሙሉ ያዘ፤ እንደ ነገዳቸው አከፋፈል በመመደብም ርስት አድርጎ ለእስራኤላውያን ሰጣቸው። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።


ርስታቸውም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት፣ ለዘጠኙ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዕጣ ተከፋፈለ።


የዮሴፍ ዘሮች ኢያሱን፣ “ቍጥራችን ብዙ ነው፤ እግዚአብሔርም አብዝቶ ባርኮናል፤ ታዲያ እንዴት ርስታችን አንድ ዕጣና አንድ ድርሻ ብቻ ሆነ?” አሉት።


የሰባቱን የመሬት ክፍፍል ዝርዝር መግለጫ ጽፋችሁ ወደ እኔ ታመጡና በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ እጥልላችኋለሁ።


ሁለተኛው ዕጣ ለስምዖን ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤ ርስታቸውም ዙሪያውን በይሁዳ ነገድ ርስት የተከበበ ነበር፤


ሦስተኛው ዕጣ ለዛብሎን ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤ የርስታቸውም ድንበር እስከ ሣሪድ ይደርሳል።


አራተኛው ዕጣ ለይሳኮር ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤


ዐምስተኛ ዕጣ ለአሴር ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤


ስድስተኛው ዕጣ ለንፍታሌም ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤


ሰባተኛው ዕጣ ለዳን ነገድ በየጐሣው ወጣ፤


跟着我们:

广告


广告