Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 23:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ባላቅም በለዓምን፣ “እንዴት እንዲህ ታደርገኛለህ? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ አመጣሁህ፤ አንተ ግን ባረክሃቸው እንጂ ምንም አላደረግህልኝም!” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “ያደረግህብኝ ምንድነው? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ባላቅም በለዓምን “ይህ ያደረግህብኝ ምንድን ነው? እኔ ወደዚህ ያመጣሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነበር፤ አንተ ግን እነርሱን ከመመረቅ በቀር ምንም አላደረግህም” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን፥ “ያደ​ረ​ግ​ኽ​ብኝ ምን​ድን ነው? ጠላ​ቶ​ችን ትረ​ግ​ም​ልኝ ዘንድ ጠራ​ሁህ፤ እነ​ሆም፥ መባ​ረ​ክን ባረ​ክ​ሃ​ቸው” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ባላቅም በለዓምን፦ ያደረግህብኝ ምንድር ነው? ጠላቶቼን ትረግምልኝ ዘንድ ጠራሁህ፤ እነሆም፥ ፈጽመህ ባረክሃቸው አለው።

参见章节 复制




ዘኍል 23:11
7 交叉引用  

ይህ የሆነው እስራኤልን በምግብና ውሃ መስተንግዶ በመቀበል ፈንታ፣ በለዓም እንዲረግምላቸው በገንዘብ ስለ ገዙት ነበር። ይሁን እንጂ አምላካችን ርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው።


‘ከግብጽ የወጣ ሕዝብ የምድሩን ገጽ አጥለቅልቆታል፤ ስለዚህ መጥተህ ርገምልኝ፤ ምናልባት ልዋጋቸውና ላባርራቸው የምችለው ከዚያ በኋላ ሊሆን ይችላል።’ ”


ወሮታህን በእጅጉ እከፍላለሁ፤ የምትለውንም ሁሉ አደርጋለሁ፤ ስለዚህ መጥተህ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ።”


እርሱም መልሶ “እግዚአብሔር በአፌ ያስቀመጠውን መናገር አይገባኝምን?” አለው።


ከዚያም ባላቅ፣ በበለዓም ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እጆቹንም አጨብጭቦ እንዲህ አለው፤ “ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፤ አንተ ግን ሦስቱንም ጊዜ ባረክሃቸው።


跟着我们:

广告


广告