ዘኍል 18:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ከተቀደሰ ቍርባን የሚለየው ሁሉ ለአንተ፣ ለወንድና ለሴት ልጆችህ መደበኛ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም በእግዚአብሔር ፊት ለአንተና ለዘሮችህ ዘላለማዊ የጨው ኪዳን ነው።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 የእስራኤል ልጆች እንደ ስጦታ ከተቀደሰው ነገር ሁሉ አንሥተው ለጌታ ያቀረቡትን ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ፤ በጌታ ፊት ለአንተ ከአንተም ጋር ለዘርህ ለዘለዓለም የጨው ቃል ኪዳን ነው።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 “እስራኤላውያን ለእኔ የሚያቀርቡአቸውን ልዩ ስጦታዎች ሁሉ ለእናንተ፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻችሁ ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም ከእናንተና ከዘሮቻችሁ ሁሉ ጋር የምገባው የማይሻር የጨው ቃል ኪዳን ነው።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር የሚለዩትን የተቀደሰውን መባ ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ሰጥቼሃለሁ፤ ይህም ለአንተ ከአንተም በኋላ ለዘርህ በእግዚአብሔር ፊት የዘለዓለም ሕግና የሁልጊዜ ቃል ኪዳን ነው።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 የእስራኤል ልጆች ከተቀደሰው ነገር ሁሉ አንሥተው ለእግዚአብሔር ያቀረቡትን ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘላለም ሰጥቼሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት ለአንተ ከአንተም ጋር ለዘርህ የጨው ቃል ኪዳን ለዘላለም ነው። 参见章节 |