ዘኍል 18:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 “የተቀደሱ ስለ ሆኑ የበሬ፣ የበግ ወይም የፍየል በኵር የሆኑትን አትዋጃቸውም፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፤ ሥባቸውንም ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ ታቃጥለዋለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ነገር ግን የላም በኵራት ወይም የበግ በኵራት ወይም የፍየል በኵራት አትዋጅም፤ የተቀደሱ ናቸው፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ እርጨው፥ ስባቸውንም ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርገህ አቃጥለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 የላም፥ የበግና የፍየል በኲር ግን መዋጀት የለባቸውም፤ እነርሱ በፍጹም የእኔ ስለ ሆኑ መሥዋዕት ሆነው መቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ አፍስሱት፤ ስባቸውንም መዓዛው እኔን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት እንዲሆን በእሳት አቃጥሉት። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ነገር ግን የላሞቹን በኵራት፥ ወይም የበጎቹን በኵራት፥ የፍየሎችንም በኵራት አትቤዥም፤ ቅዱሳን ናቸውና፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፤ ስባቸውንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን መሥዋዕት ታደርገዋለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ነገር ግን የላም በኵራት ወይም የበግ በኵራት ወይም የፍየል በኵራት አትቤዥም፤ የተቀደሱ ናቸው፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፥ ስባቸውንም ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ለእሳት ቍርባን ታቃጥለዋለህ። 参见章节 |