ዘኍል 18:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 እነዚህም አንድ ወር ሲሆናቸው ሃያ ጌራ በሚመዝነው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ልክ፣ በተወሰነው በመዋጃው ዋጋ በዐምስት ሰቅል ጥሬ ብር ትዋጀዋለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ከአንድ ወር ጀምሮ የምትዋጀውን እንደ ግምትህ ትዋጀዋለህ፤ ግምቱም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አምስት ሰቅል ይሆናል፤ እርሱም ሀያ አቦሊ ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 አንድ ወር የሞላቸው ሕፃናት በይፋ በተመደበው ዋጋ መሠረት አምስት ሰቅል ጥሬ ብር የቤዛ ዋጋ ተከፍሎላቸው ሊዋጁ ይችላሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 አንድ ወር የሆነው ልጅ ዋጋው በቤተ መቅደስ ሚዛን አምስት ሰቅል ነው። ይኸውም ሃያ አቦሊ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ከአንድ ወር ጀምሮ የምትቤዠውን እንደ ግምትህ ትቤዠዋለህ፤ ግምቱም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አምስት ሰቅል ይሆናል፤ እርሱም ሀያ አቦሊ ነው። 参见章节 |