ዘኍል 16:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 የእስራኤል አምላክ እናንተን ከቀሩት እስራኤላውያን ማኅበረ ሰብ መለየቱና በእግዚአብሔር ማደሪያ አገልግሎት እንድትፈጽሙ ወደ ራሱ ማቅረቡ፣ እንድታገለግሏቸውም በማኅበረ ሰቡ ፊት እንድትቆሙ ማድረጉ አይበቃችሁምን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር የለያችሁ፥ የጌታንም ማደሪያ አገልግሎት እንድትሠሩ፥ እንድታገለግሉአቸውም በማኅበሩ ፊት እንድትቆሙ ወደ እርሱ ለማቅረብ መፍቀዱን እንደ ቀላል ነገር ቈጠራችሁትን? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ወደ እርሱ ቀርባችሁ በማደሪያው ድንኳን አገልግሎታችሁን እንድትፈጽሙና በፊታቸውም ቆማችሁ የእስራኤልን ጉባኤ እንድታገለግሉ የእስራኤል አምላክ ከሌላው የእስራኤል ማኅበር መካከል መርጦ እናንተ የተለያችሁ እንድትሆኑ ማድረጉን እንደ ቀላል ነገር ታዩታላችሁን? 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር ለይቶ የመረጣችሁን፥ የእግዚአብሔርን ድንኳን አገልግሎት ትሠሩ ዘንድ፥ እንድታገለግሉአቸውም በማኅበሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀረባችሁን ታሳንሱታላችሁን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር የለያችሁ፥ የእግዚአብሔርንም ማደሪያ አገልግሎት ትሠሩ ዘንድ፥ እንድታገለግሉአቸውም በማኅበሩ ፊት ትቆሙ ዘንድ ወደ እርሱ ያቀረባችሁ አይበቃችሁምን? 参见章节 |