Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 16:48 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 እርሱም በሕይወት ባሉትና በሞቱት መካከል ቆመ፤ መቅሠፍቱም ተከለከለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 በሙታንና በሕያዋን መካከል ቆመ፤ መቅሠፍቱም ተገታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 በዚህም መቅሠፍቱ እንዲቆም አደረገ፤ አሮንም በሞቱትና በሕይወት ባሉት መካከል ቆሞ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 በሙ​ታ​ንና በሕ​ያ​ዋን መካ​ከል ቆመ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ቱም ተከ​ለ​ከለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 በሙታንና በሕያዋን መካከል ቆመ፤ መቅሠፍቱም ተከለከለ።

参见章节 复制




ዘኍል 16:48
14 交叉引用  

ዳዊትም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ። ከዚያም እግዚአብሔር ስለ ምድሪቱ የቀረበውን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የመጣውም መቅሠፍት ቆመ።


ፊንሐስም ተነሥቶ ጣልቃ ገባ፤ መቅሠፍቱም ተገታ፤


እያንዳንዱ ሰው ጥናውን በመያዝ ፍም አድርጎበት፣ ዕጣን ጨምሮበት ከሙሴና ከአሮን ጋራ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቆመ።


እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ የሚያጥኑትን ሁለት መቶ ዐምሳ ሰዎች በላቻቸው።


ስለዚህ አሮን፣ ሙሴ በነገረው መሠረት ወደ ማኅበሩ መካከል ሮጦ ገባ፤ መቅሠፍቱም ቀደም ብሎ በሕዝቡ መካከል መስፋፋት ጀምሮ ነበር፤ ሆኖም አሮን ዕጣኑን ዐጥኖ አስተሰረየላቸው።


ይሁን እንጂ በቆሬ ምክንያት የሞቱትን ሳይጨምር ዐሥራ አራት ሺሕ ሰባት መቶ ሰዎች ተቀሥፈው ሞቱ።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ያን ሰው በቤተ መቅደስ አግኝቶ፣ “እነሆ፣ ተፈውሰሃል፤ ከእንግዲህ ግን ኀጢአት አትሥራ፤ አለዚያ ከዚህ የባሰ ይደርስብሃል” አለው።


ደግሞም ከሙታን ያስነሣውንና ከሰማይ የሚመጣውን ልጁን፣ ከሚመጣውም ቍጣ የሚያድነንን ኢየሱስን እንዴት እንደምትጠባበቁ ይናገራሉ።


ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።


跟着我们:

广告


广告