Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 16:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ከጩኸታቸውም የተነሣ በአካባቢያቸው የነበሩት እስራኤላውያን ሁሉ፣ “ምድሪቱ እኛንም እኮ ልትውጠን ነው” ብለው ሸሹ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 “ምድሪቱ እኛንም ደግሞ እንዳትውጠን” ብለው በዙሪያቸው የነበሩ የእስራኤል ልጆች ሁሉ ከእነርሱ ጩኸት የተነሣ ሸሹ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 በዚያ የነበሩት የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የእነዚያን ሰዎች ጩኸት በሰሙ ጊዜ ሸሹ፤ “ምድር እኛንም ልትውጠን ስለምትችል እንሩጥ!” እያሉም ጮኹ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 በዙ​ሪ​ያ​ቸው የነ​በሩ የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ከጩ​ኸ​ታ​ቸው የተ​ነሣ፥ “ምድ​ሪቱ እን​ዳ​ት​ው​ጠን” ብለው ሸሹ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 በዙሪያቸው የነበሩ የእስራኤል ልጆች ሁሉ ከጩኸታቸው የተነሣ፦ ምድሪቱ እንዳትውጠን ብለው በረሩ።

参见章节 复制




ዘኍል 16:34
6 交叉引用  

ሕዝቦች በድምፅህ ነጐድጓድ ይሸሻሉ፤ መንግሥታት ስትነሣ ይበተናሉ።


እናንተም በእግዚአብሔር ተራራ ሸለቆ በኩል በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን በምድር ትሸሻላችሁ፤ ሸለቆው እስከ አጸል ይደርሳልና። በምድር መናወጥ ምክንያት ሸሽታችሁ እንደ ነበረ ትሸሻላችሁ፤ ከዚያም አምላኬ እግዚአብሔር ይመጣል፤ ቅዱሳኑም ሁሉ ዐብረውት ይመጣሉ።


እነርሱም ካላቸው ከማናቸውም ነገር ጋራ ከነሕይወታቸው ወደ መቃብር ወረዱ፤ ምድሪቱም በላያቸው ተከደነችባቸው፤ ጠፉ፤ ከማኅበረ ሰቡም ተወገዱ።


እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ የሚያጥኑትን ሁለት መቶ ዐምሳ ሰዎች በላቻቸው።


跟着我们:

广告


广告