Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 15:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ከዚያም ካህኑ፣ ባለማወቅ ኀጢአት ሠርቶ ለተሳሳተው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፤ ስርየት በሚደረግለትም ጊዜ ሰውየው ይቅር ይባላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ባለማወቅም ኃጢአት ሠርቶ ስሕተትን ለፈጸመው ለዚያ ሰው እንዲያስተሰርይለት፥ ካህኑ በጌታ ፊት ማስተስሪያ ያደርጋል፤ እርሱም ይቅር ይባላል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ካህኑ በስሕተት ኃጢአት ለሠራው ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያስተስርይለት፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ካህ​ኑም ባለ​ማ​ወቅ ስለ በደ​ለው ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ባለ​ማ​ወ​ቅም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ስለ ሠራው ሰው ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ኃጢአት ሠርቶ ሳያውቅ፥ ለሳተ ለዚያ ሰው ካህኑ ያስተሰርይለታል፤ በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፥ ይሰረይለትማል።

参见章节 复制




ዘኍል 15:28
5 交叉引用  

ካህኑም በመዳፉ ላይ የቀረውን ዘይት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያድርግ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ያስተስርይለት።


“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፤ ‘ማንም ሰው ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸውም አንዱን ተላልፎ ቢገኝ፤


ለኀጢአት መሥዋዕት ባቀረበው ወይፈን ላይ እንዳደረገው ሁሉ፣ በዚህኛውም ወይፈን ያድርግ፤ በዚህም መሠረት ካህኑ ስለ ሕዝቡ ያስተሰርያል፤ እነርሱም ይቅር ይባላሉ።


ሥቡ ከኅብረት መሥዋዕት ጠቦት በወጣበት አኳኋን ሥቡን ሁሉ ያውጣ፤ ካህኑም በመሠዊያው ላይ ለእግዚአብሔር በእሳት በሚቀርበው መሥዋዕት ላይ ያቃጥለው። በዚህ መሠረት ሰውየው የሠራውን ኀጢአት ካህኑ ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል።


ያገር ተወላጅ እስራኤላዊ ይሁን ወይም መጻተኛ ባለማወቅ ኀጢአት ከሠራ በማናቸውም ሰው ላይ ሕጉ እኩል ተፈጻሚነት ይኖረዋል።


跟着我们:

广告


广告