Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 15:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ለሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ መጻተኛ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም ሰው በእሳት የሚቀርብ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ልክ እናንተ እንደምታደርጉት ያድርግ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 መጻተኛም ከእናንተ ጋር ቢቀመጥ፥ ወይም በትውልዳችሁ መካከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ቢያቀርብ፥ እናንተ እንደምታደርጉት እርሱ እንዲሁ ያደርጋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከእናንተ ጋር ያለ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ ቊርባን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቢፈልግ፥ ይህንኑ የሥርዓት መመሪያ በተመሳሳይ ሁኔታ መከተል ይኖርበታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 መጻ​ተ​ኛም ከእ​ና​ንተ ጋር ቢቀ​መጥ፥ ወይም በት​ው​ል​ዳ​ችሁ መካ​ከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ቍር​ባን በእ​ሳት ቢያ​ቀ​ርብ እና​ንተ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን እርሱ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 መጻተኛም ከእናንተ ጋር ቢቀመጥ፥ ወይም በትውልዳችሁ መካከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ቍርባን በእሳት ቢያቀርብ፥ እናንተ የምታደርጉትን እርሱ እንዲሁ ያደርጋል።

参见章节 复制




ዘኍል 15:14
5 交叉引用  

ሰዎች ከሩቅ የመጣው ስለ ታላቁ ስምህ፣ ስለ ጠንካራዪቱ እጅህ፣ ስለ ተዘረጋችው ክንድህ ሰምቶ ነውና፤ እንግዳው መጥቶ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢጸልይ፣


“ለአሮን፣ ለልጆቹና ለእስራኤላውያን በሙሉ እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ከእናንተ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር መጻተኛ ስእለት ለመፈጸም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማበርከት ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርብ ቢሆን፣


እንደነዚህ ያሉትን እንስሳት ከባዕዳን በመቀበል ለአምላካችሁ ምግብ አድርጋችሁ አታቅርቡ፤ ነውር ስላለባቸው ፍጹም አይደሉምና ተቀባይነት አይኖራቸውም።’ ”


“ ‘ማንኛውም የአገር ተወላጅ የሆነ በእሳት የሚቀርብ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ እነዚህን ነገሮች በዚሁ ሁኔታ ያድርግ።


ማኅበረ ሰቡ ለእናንተም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖር መጻተኛ አንድ ዐይነት ደንብ ይኖረዋል፤ ይህም በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ የማይሻር ሥርዐት ነው። እናንተም ሆናችሁ መጻተኞቹ በእግዚአብሔር ፊት እኩል ትታያላችሁ፤


跟着我们:

广告


广告