ዘኍል 11:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 በግብጽ ያለ ምንም ዋጋ የበላነው ዓሣ እንዲሁም ዱባው፣ በጢኹ፣ ኵራቱ፣ ነጭ ሽንኵርቱ ትዝ ይለናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 በግብጽ ሳለን እንዲያው በነጻ እንበላው የነበረውን ዓሣ፥ ዱባውንም፥ ሐብሐብውንም፥ ባሕሮውንም፥ ቀዩንም ሽንኩርት፥ ነጩንም ሽንኩርት እናስታውሳለን፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 በግብጽ ሳለን ምንም ዋጋ ሳንከፍል የፈለግነውን ያኽል ዓሣ እንበላ እንደ ነበረ እናስታውሳለን፤ በዚያ ሳለን እንበላ የነበረውን ዱባ፥ (ኪያር) ሀብሀብ (በጢኽ)፥ ኲራት (ድንች መሳይ ምግብ) ቀዩንና ነጩን ሽንኩርት፥ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 በግብፅ ያለ ዋጋ እንበላው የነበረውን ዓሣ፥ ዳቦውንም፥ በጢኹንም፥ ኩራቱንም፥ ቀዩንም ሽንኩርት፥ ነጩንም ሽንኩርት ቍንዶ በርበሬውንም እናስባለን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 በግብፅ ያለ ዋጋ እንበላው የነበረውን ዓሣ፥ ዱባውንም፥ በጢኹንም፥ ኩራቱንም፥ ቀዩንም ሽንኩርት፥ ነጩንም ሽንኩርት እናስባለን፤ 参见章节 |