ዘኍል 11:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “እነሆ እኔ በስድስት መቶ ሺሕ እግረኛ መካከል እገኛለሁ፤ አንተ ደግሞ ‘ወር ሙሉ የሚበሉትን ሥጋ እኔ እሰጣቸዋለሁ’ ብለሃል፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ነገር ግን ሙሴ እንዲህ አለ፦ “እኔ በመካከላቸው ሆኜ በእኔ ዘንድ ያሉት ሰዎች ሲቈጠሩ ስድስት መቶ ሺህ እግረኛ ናቸው፤ አንተም፦ ‘ወር ሙሉ የሚበሉትን ሥጋ እኔ እሰጣቸዋለሁ’ አልህ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ሙሴም ለእግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ ስድስት መቶ ሺህ ሕዝብ በመምራት ላይ እገኛለሁ፤ ለአንድ ወር የሚበቃ ሥጋ ልትሰጣቸው ቃል ገብተሃል፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ሙሴም፥ “እኔ በመካከላቸው ያለሁ ሕዝብ ስድስት መቶ ሺህ እግረኛ ናቸው፤ አንተም፦ ሥጋን እሰጣቸዋለሁ፥ ወር ሙሉም ይበሉታል አልህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ሙሴም፦ እኔ በመካከላቸው ያለሁ ሕዝብ ስድስት መቶ ሺህ እግረኛ ናቸው፤ አንተም፦ ወር ሙሉ የሚበሉትን ሥጋ እኔ እሰጣቸዋለሁ አልህ። 参见章节 |