ዘኍል 10:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 በመጨረሻም የዳን ሰፈር ሰራዊት ለሁሉም ክፍሎች የኋላ ደጀን በመሆን በዐርማቸው ሥር ተጓዙ፤ አለቃቸውም የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ሰፈሮቹንም ሁሉ ከኋላ ሆኖ የሚጠብቀው የዳን ልጆች ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር አለቃ ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 በመጨረሻም በዳን ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙትና ለሁሉም ክፍሎች ደጀን የሚሆኑት በዓሚሻዳይ ልጅ በአሒዔዜር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ከሠራዊቱ ሁሉ በኋላ የዳን ልጆች ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊታቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚሳዲ ልጅ አኪያዜር አለቃ ነበረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ከሰፈሮቹ ሁሉ በኋላ የሆነ የዳን ልጆች ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር አለቃ ነበረ። 参见章节 |