Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 7:63 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

63 ከካህናቱ መካከል፦ የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቷል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

63 ከካህናቱም የሐባያ ልጆች፥ የሃቆጽ ልጆች፥ የባርዚላይ ልጆች እሱም ከገለዓዳዊው የባርዚላይ ሴቶች ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስማቸውም የተጠራ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

63-64 ከዚህ የሚከተሉት የካህናት ጐሣዎች የቀድሞ አባቶቻቸውን የትውልድ ሐረግ ለማረጋገጥ አልቻሉም፤ እነርሱም ሖባያ፥ ሀቆጽና ባርዚላይ ናቸው፤ የካህን ወገን የሆነው የባርዚላይ የቀድሞ አባት የገለዓድ ተወላጅ ከነበረው ከባርዚላይ ወገን አንዲት ሴት አግብቶ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ የዐማቱን ጐሣ ስም ወርሶ ይኖር ነበር፤ የቀድሞ አባቶቻቸውንም የትውልድ ሐረግ ለማረጋገጥ ካለመቻላቸው የተነሣ፥ በክህነት ለማገልገል አልተፈቀደላቸውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

63 ከካ​ህ​ና​ቱም የአ​ብያ ልጆች፥ የአ​ቆስ ልጆች፥ ከገ​ለ​ዓ​ዳ​ዊው ከቤ​ር​ዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስ​ሙም የተ​ጠራ የቤ​ር​ዜሊ ልጆች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

63 ከካህናቱም የኤብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ በስሙም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች።

参见章节 复制




ነህምያ 7:63
8 交叉引用  

ዳዊት መሃናይም ሲደርስ፣ ከአሞናውያን ከተማ ከረባት የመጣው፣ የናዖስ ልጅ ሾቢ፣ ከሎደባር የመጣው የዓሚኤል ልጅ ማኪርና ከሮግሊም የመጣው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ


“ከወንድምህ ከአቤሴሎም በሸሸሁ ጊዜ መልካም ነገር አድርገውልኛልና ለገለዓዳዊው ለቤርዜሊ ልጆች ግን በጎ ነገር አድርግላቸው፤ ማእድህን ከሚካፈሉ ሰዎችም ጋራ ዐብረው ይብሉ።


የቆጽ ወንዶች ልጆች ዓኑብ፣ ጾቤባና፣ የሃሩም ልጅ የአሐርሔል ጐሣዎች ናቸው።


የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ። ከርሱ ቀጥሎ ያለውን የሜሴዜቤል ልጅ የቤራክያ ልጅ ሜሱላም መልሶ ሠራ። ከርሱ ቀጥሎ ያለውን የበዓና ልጅ ሳዶቅ መልሶ ሠራ፤


የዳላያ፣ የጦብያና፣ የኔቆዳ ዘሮች 642


እነዚህ በትውልድ መዝገቡ ውስጥ የቤተ ሰባቸውን ዝርዝር ፈለጉ፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤ ስለዚህ እንዳልነጹ ተቈጥረው ከክህነት ተከለከሉ።


跟着我们:

广告


广告