Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 7:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ከወሰዳቸው ምርኮኞች መካከል የተመለሱት የአውራጃው ተወላጆች እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ወደሚገኙት ወደ የራሳቸው ከተሞች ተመለሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ ገዛ ከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከምርኮኞች ብዙዎቹ ከባቢሎን አውራጃዎች ተነሥተው፥ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ምድር በመመለስ፥ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ከተማው ገብቶአል፤ ናቡከደነፆር ከወሰዳቸው ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው በባቢሎን ምድር ይኖሩ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው።

参见章节 复制




ነህምያ 7:6
10 交叉引用  

የክብር ዘቡ አዛዥ ናቡዘረዳን ድኾችንና በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብና ሸሽተው ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን አፈለሳቸው።


የታላቁ አምላክ ቤተ መቅደስ ወደሚገኝበት ወደ ይሁዳ አውራጃ ሄደን እንደ ነበር በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን በታላላቅ ድንጋዮች እየገነቡና ቅጥሩንም በወፍራም ምሰሶዎች እየሠሩ ነው፤ ሥራው በትጋት በመከናወንና በእነርሱም አመራር በመፋጠን ላይ ይገኛል።


በሜዶን አውራጃ በሚገኘው በአሕምታ ከተማ አንድ ጥቅልል ብራና ተገኘ፤ በውስጡም እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎበት ነበር፤ ማስታወሻ፤


እነርሱም፣ “በሕይወት ተርፈው ከምርኮ ወደ አገራቸው የተመለሱት ሰዎች በታላቅ መከራና ውርደት ላይ ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌም ቅጥር ፈራርሷል፤ በሮቿም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።


የመጡትም ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከዓዛርያስ፣ ከረዓምያ፣ ከነሐማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከበላሳን፣ ከሚስጴሬት፣ ከበጉዋይ፣ ከነሑምና ከበዓና ጋራ ነው። የእስራኤል ሰዎች ዝርዝር፦


跟着我们:

广告


广告