Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 7:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ለእነርሱም፣ “የኢየሩሳሌም በሮች ፀሓይ ሞቅ እስክትል ድረስ አይከፈቱም፤ በር ጠባቂዎቹ ዘብ በሚቆሙበት ጊዜ ሁሉ፣ በሮቹን ይዝጓቸው፤ መወርወሪያም ያድርጉባቸው፣ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዶቹን በየጥበቃ ቦታቸው፣ አንዳንዶቹን ደግሞ በየቤታቸው አጠገብ እንዲቆሙ መድቡ” አልኋቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እኔም እንዲህ አልኋቸው፦ የኢየሩሳሌም በሮች ፀሐይ ሞቅ እስኪል ድረስ አይከፈቱ፥ በሚቆሙበት ጊዜ በሮቹን ይዝጉ፥ ይቆልፉትም፤ ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዱን በተራው አንዳንዱን ደግሞ በየቤቱ አጠገብ ጠባቂዎች ይሾሙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ለእነርሱም የሰጠኋቸው መመሪያ የኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ፀሐይ እስኪሞቅ ድረስ እንዳይከፈቱ፥ ደግሞ ማታ ፀሐይ ስትጠልቅ የዘብ ጠባቂዎቹ ከመሄዳቸው በፊት የቅጽር በሮቹ በቊልፍና በመወርወሪያ አጥብቀው እንዲዘጉአቸው ነበር። እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች መካከል ሰዎችን ቀጥረው ከፊሎቹ በሥራቸው ላይ ሆነው ሌሎቹ ደግሞ በየቤታቸው ፊት ለፊት ሆነው እንዲጠብቁ አዘዝኳቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እኔም፥ “ፀሐይ እስ​ኪ​ሞቅ ድረስ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሮች አይ​ከ​ፈቱ፤ እነ​ር​ሱም ቆመው ሳሉ ደጆ​ቹን ይዝጉ፤ ይቈ​ል​ፉም፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሰዎች አን​ዳ​ን​ዱን በየ​ተ​ራው፥ አን​ዳ​ን​ዱ​ንም በየ​ቤቱ አን​ጻር ጠባ​ቂ​ዎ​ችን አስ​ቀ​ምጡ” አል​ኋ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እኔም፦ ፀሀይ እስኪሞቅ ድረስ የኢየሩሳሌም በሮች አይከፈቱ፥ እነርሱም ቆመው ሳሉ ደጆቹን ይዝጉ፥ ይቈልፉም፥ ከኢየሩሳሌምም ሰዎች አንዳንዱን በየተራው አንዳንዱንም በየቤቱ አንጻር ጠባቆችን አስቀምጡ አልኋቸው።

参见章节 复制




ነህምያ 7:3
8 交叉引用  

በሰንበት ዋዜማ በኢየሩሳሌም በሮች ላይ የምሽቱ ጥላ ማረፍ ሲጀምር በሮቹ እንዲዘጉና፣ ሰንበት እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ፤ በሰንበት ቀን ጭነት እንዳይገባም ከራሴ ሰዎች አንዳንዶቹን በየበሩ ላይ አቆምሁ።


ከእነርሱ ቀጥሎ ብንያምና አሱብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን መልሰው ሠሩ፤ ከእነርሱም ቀጥሎ የሐናንያ ልጅ የመዕሤያ ልጅ ዓዛርያስ በቤቱ አጠገብ ያለውን መልሶ ሠራ።


በኢየሩሳሌምም ላይ ወንድሜን አናኒን እንዲሁም ፍጹም ታማኝና ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይበልጥ የሚፈራውን የግንቡን አዛዥ ሐናንያን ኀላፊ አደረግኋቸው።


ከተማዪቱ ታላቅና ሰፊ ነበረች፤ የሚኖርባት ሕዝብ ግን ጥቂት ሲሆን፣ ቤቶች ገና አልተሠሩባትም ነበር።


እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።


እርሱ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና፤ ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኳል።


“እንግዲህ፣ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልኆች እንደ ርግብ የዋሃን ሁኑ።


跟着我们:

广告


广告