Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 6:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከዚህም በተጨማሪ ስለ መልካም ሥራው በየጊዜው ይነግሩኝና እኔም ያልሁትን ይነግሩት ነበር፤ ጦቢያም እኔን ለማስፈራራት ደብዳቤ ይልክብኝ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በተጨማሪም መልካም ሥራውን በፊቴ ይናገሩ ነበር፥ እኔ ያልሁትንም ለእርሱ ይነግሩት ነበር፤ ጦቢያም ሊያስፈራራኝ ደብዳቤዎችን ይልክ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ጦቢያ ያደረገውን መልካም ነገር በማጋነን በፊቴ እንኳ ሳይቀር ይናገሩለት ነበር፤ እኔም የምለውን ሁሉ ለእርሱ ይነግሩት ነበር፤ ከዚህም የተነሣ እርሱ እኔን ለማስፈራራት ደብዳቤዎችን ከመላክ አልተቈጠበም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ደግ​ሞም በፊቴ ስለ እርሱ መል​ካ​ም​ነት ይና​ገሩ ነበር፤ የእ​ር​ሱን ነገር ወደ እኔ ያመጡ ነበር፤ የእ​ኔ​ንም ቃል ወደ እርሱ ይወ​ስዱ ነበር፤ ጦቢ​ያም ሊያ​ስ​ፈ​ራ​ራኝ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን ይልክ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ደግሞም በፊቴ ስለ እርሱ መልካም ይናገሩ ነበር፥ ቃሌንም ያወሩለት ነበር፥ ጦብያም ሊያስፈራራኝ ደብዳቤዎችን ይልክ ነበር።

参见章节 复制




ነህምያ 6:19
10 交叉引用  

በገንዘብ የተገዛው እኔን ለማስፈራራት ነው፤ ይኸውም ይህን በመፈጸም ኀጢአት እንድሠራና በዚህም መጥፎ ስም ሰጥተው ተቀባይነት እንዳይኖረኝ ለማድረግ ነው።


በይሁዳ የሚኖሩ ሰዎች ምለውለት ነበር፤ ምክንያቱም የኤራ ልጅ የሴኬንያ ዐማት ከመሆኑም በላይ ልጁ ዮሐናን የቤራክያን ልጅ የሜሱላምን ሴት ልጅ አግብቶ ነበር።


ሁሉም፣ “እጃቸው መሥራት እስኪሳነው ድረስ ይዝላል፤ ሥራውም ሳይጠናቀቅ ይቀራል” ብለው በማሰብ ሊያስፈራሩን ሞከሩ። እኔ ግን፣ “አሁንም እጄን አበርታ” ስል ጸለይሁ።


ቅጥሩ እንደ ገና ከተሠራና መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ከገጠምሁ በኋላ፣ በር ጠባቂዎች፣ መዘምራንና ሌዋውያን ተመደቡ።


ሕግን የሚተዉ ክፉዎችን ያወድሳሉ፤ ሕግን የሚጠብቁ ግን ይቋቋሟቸዋል።


ከዓለም ብትሆኑ ኖሮ፣ ዓለም የራሱ እንደ ሆኑት አድርጎ በወደዳችሁ ነበር፤ ከዓለም ለይቼ ስለ መረጥኋችሁ የዓለም አይደላችሁም፤ ዓለም የሚጠላችሁም ስለዚሁ ነው።


ዓለም እናንተን ሊጠላ አይችልም፤ እኔ ግን፣ አድራጎቱ ክፉ መሆኑን ስለምመሰክርበት ይጠላኛል።


እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ የሚናገሩት እንደ ዓለም ነው፤ ዓለምም ይሰማቸዋል።


跟着我们:

广告


广告