Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 6:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በይሁዳ የሚኖሩ ሰዎች ምለውለት ነበር፤ ምክንያቱም የኤራ ልጅ የሴኬንያ ዐማት ከመሆኑም በላይ ልጁ ዮሐናን የቤራክያን ልጅ የሜሱላምን ሴት ልጅ አግብቶ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በይሁዳ ለእርሱ የማሉለት ብዙ ሰዎች ነበሩና፤ የአራሕ ልጅ የሼካንያ አማች ነበረና፥ ልጁ ይሆሐናንም የቤራክያን ልጅ የሜሹላምን ሴት ልጅ አግብቷልና።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ጦብያ የአ​ራሄ ልጅ የሴ​ኬ​ንያ አማች ስለ ነበረ፥ ልጁም ዮሐ​ናን የቤ​ራ​ክ​ያን ልጅ የሜ​ሱ​ላ​ምን ሴት ልጅ ስላ​ገባ፥ በይ​ሁዳ ብዙ ሰዎች ከእ​ርሱ ጋር ተማ​ም​ለው ነበ​ርና።

参见章节 复制




ነህምያ 6:18
7 交叉引用  

የሐናንያ ዘሮች፤ ፈላጥያ፣ የሻያ፤ እንዲሁም የረፋያ፣ የአርናን፣ የአብድዩና የሴኬንያ ወንዶች ልጆች።


የኤራ ዘሮች 775


ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ሌላ ክፍል ደግሞ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛ ልጅ ሐኖን መልሰው ሠሩ። ከእነርሱም ቀጥሎ የቤራክያ ልጅ ሜሱላም ከመኖሪያው ትይዩ ያለውን መልሶ ሠራ።


የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ። ከርሱ ቀጥሎ ያለውን የሜሴዜቤል ልጅ የቤራክያ ልጅ ሜሱላም መልሶ ሠራ። ከርሱ ቀጥሎ ያለውን የበዓና ልጅ ሳዶቅ መልሶ ሠራ፤


በዚያ ጊዜ የይሁዳ መኳንንት ለጦቢያ ብዙ ደብዳቤ ይልኩ ነበር፤ ከጦቢያም መልስ ይላክላቸው ነበር።


ከዚህም በተጨማሪ ስለ መልካም ሥራው በየጊዜው ይነግሩኝና እኔም ያልሁትን ይነግሩት ነበር፤ ጦቢያም እኔን ለማስፈራራት ደብዳቤ ይልክብኝ ነበር።


የኤራ ዘሮች 652


跟着我们:

广告


广告