Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 4:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሕዝቡ ከልቡ ስለሚሠራ፣ ቅጥሩን እኩሌታው ድረስ መልሰን ሠራነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በአጠገባቸው የተቀመጡ አይሁድ መጥተው፦ “ከስፍራው ሁሉ ይመጡብናል” ብለው ዐሥር ጊዜ ነገሩን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እኛም ቅጽሩን መልሶ የማነጹን ሥራ ቀጠልን፤ ሕዝቡ በትጋት በመሥራቱ ሥራው እየተፋጠነ ሄዶ ግማሽ ደረሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ቅጥ​ሩ​ንም ሠራን፤ ቅጥ​ሩም ሁሉ እስከ እኩ​ሌ​ታው ድረስ ተጋ​ጠመ፤ ሕዝቡ ከልብ ይሠራ ነበ​ርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ቅጥሩንም ሠራን፥ ቅጥሩም ሁሉ እስከ እኩሌታው ድረስ ተጋጠመ፥ የሕዝቡም ልብ ለሥራው ጨከነ።

参见章节 复制




ነህምያ 4:6
13 交叉引用  

“ሁሉ የተገኘው ከአንተ ነው፤ ለአንተም የሰጠንህ ከእጅህ የተቀበልነውን ብቻ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለ ቸርነት እናደርግ ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማነው?


ከዚህም በቀር ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር የተነሣ፣ ለዚህ ለተቀደሰ ቤት ከዚህ በፊት ከሰጠሁት በተጨማሪ፣ ለዚሁ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የግል ሀብቴ የሆነውን ወርቅና ብር እሰጣለሁ፤


ሕዝቅያስና ሕዝቡ፣ ነገሩ ሁሉ እንዲህ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲከናወን እግዚአብሔር ስለ ረዳቸው ሐሤት አደረጉ።


የፈረሰውን በሚሠሩት ፊት የስድብ ናዳ አውርደዋልና በደላቸውን ይቅር አትበል፤ ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አታጥፋው።


ሰንባላጥ፣ ጦቢያ፣ ዐረቦች፣ የአሞንና የአሽዶድ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌም ቅጥር ሥራ እየተፋጠነና ክፍት ቦታዎቹም ሁሉ እየተሞሉ መሆናቸውን በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ።


ቅጥሩም ኤሉል በተባለው ወር ሃያ ዐምስተኛ ቀን፣ በዐምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጠናቀቀ።


ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ ከንጋት ማሕፀን፣ በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣ የጕልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ።


ኢየሩሳሌም እጅግ እንደ ተጠጋጋች፣ ከተማ ሆና ተሠርታለች።


ስለዚህ እግዚአብሔር የይሁዳን ገዥ፣ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፣ የሊቀ ካህናቱን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስና ከምርኮ የተረፈውን ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አነሣሣ፤ እነርሱም መጥተው የአምላካቸውን የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ።


እንደ በጎ ፈቃዱ መፈለግንና ማድረግን በእናንተ ውስጥ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።


ፈቃዱን እንድታደርጉ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ ደስ የሚያሠኘውንም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ያድርግ፤ ለርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን። አሜን።


跟着我们:

广告


广告