Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 3:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ። ከርሱ ቀጥሎ ያለውን የሜሴዜቤል ልጅ የቤራክያ ልጅ ሜሱላም መልሶ ሠራ። ከርሱ ቀጥሎ ያለውን የበዓና ልጅ ሳዶቅ መልሶ ሠራ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በአጠገባቸውም የቆጽ ልጅ የኡሪያ ልጅ ሜሬሞት አደሰ። በአጠገባቸውም የመሼዛቤል ልጅ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም አደሰ። በአጠገባቸውም የባዓና ልጅ ጻዶቅ አደሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የሀቆጽ የልጅ ልጅ የሆነው የኡሪያ ልጅ መሬሞት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። (አደሰ ቢሆን ይመረጣል) የመሼዛቤል የልጅ ልጅ የሆነው የበራክያ ልጅ መሹላም ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ፤ ከዚያም ቀጥሎ የሚገኘውን ክፍል የበዓና ልጅ ሳዶቅ ሠራው። (አደሰ ቢሆን ይመረጣል)

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የቆስ ልጅ የኡ​ርያ ልጅ ሚራ​ሞት ይሠራ ጀመረ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የሜ​ሴ​ዜ​ቤል ልጅ የበ​ራ​ክያ ልጅ ሜሱ​ላም ይሠራ ጀመረ። በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የበ​ሃና ልጅ ሳዶቅ ይሠራ ጀመረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በአጠገባቸውም የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት አደሰ። በአጠገባቸውም የሜሴዜቤል ልጅ የበራክያ ልጅ ሜሱላም አደሰ። በአጠገባቸውም የበዓና ልጅ ሳዶቅ አደሰ።

参见章节 复制




ነህምያ 3:4
11 交叉引用  

ከካህናቱ መካከል፦ የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቷል።


በአራተኛው ቀን ብሩን፣ ወርቁንና ንዋያተ ቅድሳቱን በአምላካችን ቤት መዝነን ለኦርዮ ልጅ ለካህኑ ለሜሪሞት በእጁ አስረከብነው፤ ከርሱም ጋራ የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር፣ ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ።


ቡኒ፣ ዓዝጋድ፣ ቤባይ፣


ሜሴዜቤል፣ ሳዶቅ፣ ያጹአ፣


ሜሱላም፣ አብያ፣ ሚያሚን፣


ከርሱ ቀጥሎ ከኤልያሴብ ቤት መግቢያ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ያለውን ሌላ ክፍል የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት መልሶ ሠራ።


የዓሣ በሩን የሃስናአ ልጆች ሠሩ፤ እነርሱም ምሰሶዎቹን አቁመው መዝጊያዎቹን፣ መቀርቀሪያዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ።


ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ሌላ ክፍል ደግሞ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛ ልጅ ሐኖን መልሰው ሠሩ። ከእነርሱም ቀጥሎ የቤራክያ ልጅ ሜሱላም ከመኖሪያው ትይዩ ያለውን መልሶ ሠራ።


የሚቀጥለውን ክፍል የቴቁሔ ሰዎች መልሰው ሠሩ፤ መኳንንታቸው ግን በተቈጣጣሪ አሠሪዎቻቸው ሥር ሆነው በሥራው መጠመድ አልፈለጉም።


በይሁዳ የሚኖሩ ሰዎች ምለውለት ነበር፤ ምክንያቱም የኤራ ልጅ የሴኬንያ ዐማት ከመሆኑም በላይ ልጁ ዮሐናን የቤራክያን ልጅ የሜሱላምን ሴት ልጅ አግብቶ ነበር።


ከካህናቱ መካከል፦ የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቷል።


跟着我们:

广告


广告