Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 3:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከርሱ ቀጥሎ ከኤልያሴብ ቤት መግቢያ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ያለውን ሌላ ክፍል የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት መልሶ ሠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከእርሱም በኋላ የቆጽ ልጅ የኡሪያ ልጅ ሜሬሞት ከኤልያሺብ ቤት በር ጀምሮ እስከ ኤልያሺብ ቤት መጨረሻ ድረስ ያለውን ክፍል አደሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የሀቆጽ የልጅ ልጅ የሆነው የኡሪያ ልጅ መሬሞት እስከ ኤልያሺብ ቤት መጨረሻ ያለውን ሠራ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ከእ​ር​ሱም በኋላ የአ​ቆስ ልጅ የኡ​ርያ ልጅ ሚራ​ሞት ከኤ​ል​ያ​ሴብ ቤት መግ​ቢያ ጀምሮ እሰከ ኤል​ያ​ሴብ ቤት መጨ​ረሻ ድረስ ሌላ​ውን ክፍል ሠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ከእርሱም በኋላ የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት ከኤልያሴብ ቤት መግቢያ ጀምሮ እስከ ኤልያሴብ ቤት መጨረሻ ድረስ ሌላውን ክፍል አደሰ።

参见章节 复制




ነህምያ 3:21
8 交叉引用  

የቆጽ ወንዶች ልጆች ዓኑብ፣ ጾቤባና፣ የሃሩም ልጅ የአሐርሔል ጐሣዎች ናቸው።


ከካህናቱ መካከል፦ የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቷል።


በአራተኛው ቀን ብሩን፣ ወርቁንና ንዋያተ ቅድሳቱን በአምላካችን ቤት መዝነን ለኦርዮ ልጅ ለካህኑ ለሜሪሞት በእጁ አስረከብነው፤ ከርሱም ጋራ የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር፣ ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ።


ሊቀ ካህናቱ ኤልያሴብና ወንድሞቹ ካህናት ለሥራ ተነሡ፤ የበጎች በር የተባለውንም እንደ ገና ሠሩ። ቀደሱት፤ መዝጊያዎቹንም በየቦታቸው ላይ አቆሙ። መቶ ግንብ እስከሚባለው ግንብና ሐናንኤል ግንብ ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ሠርተው ቀደሱት፤


ከርሱም ቀጥሎ የዘካይ ልጅ ባሮክ ከማእዘኑ ጀምሮ እስከ ሊቀ ካህኑ እስከ ኤልያሴብ ቤት መግቢያ ያለውን ሌላ ክፍል በትጋት መልሶ ሠራ።


ከርሱም ቀጥሎ ያለውን ክፍል ከአካባቢው የመጡት ካህናት መልሰው ሠሩ።


የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ። ከርሱ ቀጥሎ ያለውን የሜሴዜቤል ልጅ የቤራክያ ልጅ ሜሱላም መልሶ ሠራ። ከርሱ ቀጥሎ ያለውን የበዓና ልጅ ሳዶቅ መልሶ ሠራ፤


ከካህናቱ መካከል፦ የኤብያ፣ የአቆስ፣ የቤርዜሊ ዘሮች፤ ይህ ሰው የገለዓዳዊውን የቤርዜሊን ሴት ልጅ አግብቶ በዚሁ ስም ለመጠራት በቅቷል።


跟着我们:

广告


广告