Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 3:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የቈሻሻ መጣያ በር ተብሎ የሚጠራው የቤትሐካሪም አውራጃ ገዥ የሆነው የሬካብ ልጅ መልክያ መልሶ ሠራ፤ መልሶ ከሠራ በኋላም መዝጊያዎቹን፣ መቀርቀሪያዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የቤትሐካሪም አውራጃ ገዢ የሬካብ ልጅ ማልኪያ “የፍግ በር” አደሰ፤ መልሶ ሠራው፥ በሮቹን አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጀ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የቤትሀካሬም ወረዳ ገዢ የሆነው የሬካብ ልጅ ማልኪያ የጒድፍ መጣያውን ቅጽር በር በማደስ ሠራ፤ በሮችን ገጠመ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጀ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የቤ​ት​ሐ​ካ​ሪ​ምም ግዛት ገዢ የሬ​ካብ ልጅ መል​ክያ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹና ከል​ጆቹ ጋር የጕ​ድፍ መጣ​ያ​ውን በር ሠራ፤ ከደ​ነው፤ ሳን​ቃ​ዎ​ቹ​ንም አቆመ፤ ቍል​ፎ​ቹ​ንና መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አደ​ረገ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የቤትሐካሪምም ግዛት አለቃ የሬካብ ልጅ መልክያ የጉድፍ መጣያውን በር አደሰ፥ ሠራው፥ ሳንቃዎቹንም አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ።

参见章节 复制




ነህምያ 3:14
9 交叉引用  

በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም ከብንያም ነገድ የብኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች ነበሩ፤ ብኤሮት ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ትቈጠራለች።


ከዚያም ተነሥቶ ሲሄድ የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ወደ እርሱ ሲመጣ መንገድ ላይ አገኘው። ኢዩም ሰላምታ ሰጥቶት “ልቤ ለልብህ ታማኝ የሆነውን ያህል የአንተስ ልብ ለልቤ እንዲሁ ታማኝ ነውን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም፣ “አዎን፤ ነው!” ብሎ መለሰ። ኢዩም፣ “እንግዲያውስ እጅህን ስጠኝ” አለው። እጁንም ሰጠው፤ ከዚያም ኢዩ ደግፎ ወደ ሠረገላው አወጣው።


የሚካኤል ልጅ፣ የበዓሤያ ልጅ፣ የመልክያ ልጅ፣


እኔም የይሁዳን መሪዎች በቅጥሩ ግንብ ዐናት ላይ እንዲወጡ አደረግሁ፤ ደግሞም ምስጋና እንዲያቀርቡ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን መደብሁ። አንዱ በቅጥሩ ግንብ ዐናት በስተቀኝ በኩል ቈሻሻ መጣያ በር ወደሚባለው ሄደ።


በሌሊትም ወጥቼ በሸለቆው በር በኩል አድርጌ ወደ ዘንዶው የውሃ ጕድጓድና ወደ ቈሻሻ መድፊያው በር ሄድሁ፤ የፈረሱትንም የኢየሩሳሌምን ቅጥሮችና በእሳት የወደሙትን በሮች ተመለከትሁ።


ከዚያ የሚቀጥለውን ክፍል የኢየሩሳሌም አውራጃ እኩሌታ ገዥ የሆነው የሑር ልጅ ረፋያ መልሶ ሠራ።


“እናንተ የብንያም ልጆች፤ ክፉ ነገር፣ ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ድንገት ይመጣልና፣ ከኢየሩሳሌም ሸሽታችሁ አምልጡ፤ በቴቁሔ መለከትን ንፉ፤ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ።


跟着我们:

广告


广告