ነህምያ 13:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ስለዚህ ሹማምቱን ገሥጬ፣ “ቤተ መቅደሱ እስከዚህ ቸል የተባለው ለምንድን ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው። ከዚያም እነርሱን በአንድነት ሰብስቤ ወደ ምድብ ሥራቸው እንዲመለሱ አደረግሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 እኔም፦ የእግዚአብሔር ቤት ስለምን ተተወ? ብዬ ከአለቆቹ ጋር ተከራከርሁ። ሰበሰብኋቸውም፥ በየስፍራቸውም አቆምኋቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ቤተ መቅደሱም ይህን ያኽል ቸል እስኪባል ዝም ብለው በመመልከታቸው ባለሥልጣኖችን ገሠጽኩ፤ ሌዋውያኑንና መዘምራኑንም ወደ ቤተ መቅደስ መልሼ በማምጣት ሥራቸውን እንዲቀጥሉ አደረግሁ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እኔም፥ “የእግዚአብሔር ቤት ስለ ምን ተተወ?” ብዬ ከአለቆቹ ጋር ተከራከርሁ። ሰበሰብኋቸውም፤ በየስፍራቸውም አቆምኋቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 እኔም፦ የእግዚአብሔር ቤት ስለ ምን ተተወ? ብዬ ከአለቆቹ ጋር ተከራከርሁ። ሰበሰብኋቸውም፥ በየስፍራቸውም አቆምኋቸው። 参见章节 |