Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 12:36 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ወንድሞቹ ሸማያ፣ ኤዝርኤል፣ ሚላላይ፣ ጊላላይ፣ መዓይ፣ ናትናኤል፣ ይሁዳና አናኒም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት የዜማ መሣሪያዎቹን ይዘው ሄዱ፤ ሰልፉን የሚመራውም ጸሓፊው ዕዝራ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ወንድሞቹም ሸማዕያ፥ ዓዛርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳና ሐናኒ የእግዚአብሔር ሰው የዳዊትን የዜማ መሣሪያ ይዘው ሄዱ፤ ጸሐፊው ዕዝራም በፊታቸው ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 የራሱ ጐሣ አባላት የነበሩት ሸማዕያ፥ ዐዛርኤል፥ ሚለላይ፥ ጊለላይ፥ ማዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳና ሐናኒ የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ይዘምርበት የነበረውን የሙዚቃ መሣሪያ ሁሉ ተሸክመው ተከተሉት፤ የዚህንም ቡድን ሰልፍ የሚመራው የሕግ ሊቁ ዕዝራ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ወን​ድ​ሞ​ቹም ሰማ​ዕያ፥ አዘ​ር​ኤል፥ ማዕ​ላይ፥ ጌላ​ላይ፥ መዓይ፥ ናት​ና​ኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው የዳ​ዊ​ትን የዜ​ማ​ውን ዕቃ ይዘው ሄዱ፤ ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ በፊ​ታ​ቸው ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ወንድሞቹም ሸማያ፥ ኤዝርኤል፥ ሚላላይ፥ ጊላላይ፥ መዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእግዚአብሔርን ሰው የዳዊትን የዜማውን ዕቃ ይዘው ሄዱ፥ ጸሐፊውም ዕዝራ በፊታቸው ነበረ።

参见章节 复制




ነህምያ 12:36
8 交叉引用  

አራቱ ሺሕ የቅጥሩ በር ጠባቂዎች ይሁኑ፤ አራቱ ሺሕ ደግሞ ለዚሁ ብዬ ባዘጋጀሁት የዜማ መሣሪያ እግዚአብሔርን ያመስግኑ”።


የአባቱን የዳዊትን ሥርዐት በመከተልም፣ ካህናቱን በየአገልግሎት ክፍላቸው ሌዋውያኑንም ምስጋናውን እንዲመሩና በየዕለቱ ሥራቸው ካህናቱን እንዲረዱ መደባቸው። ደግሞም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት፣ የቤተ መቅደሱን በር ጠባቂዎች በልዩ ልዩ በሮች ጥበቃ ላይ በየክፍላቸው መደባቸው።


ከእነዚህም ነገሮች በኋላ በፋርስ ንጉሥ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት፣ ዕዝራ የሠራያ ልጅ፣ የዓዛርያስ ልጅ፣ የኬልቅያስ ልጅ


በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ከባቢሎን ዐብረውኝ የወጡት የየቤተ ሰቡ አለቆችና ዐብረዋቸው የተመዘገቡት እነዚህ ናቸው፤


የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድምኤል ልጅ ኢያሱ ነበሩ፤ እነርሱም ከወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት እየተቀባበሉ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር።


እንዲሁም መለከት ከያዙ ጥቂት ካህናትና ከአሳፍ ልጅ፣ ከዛኩር ልጅ፣ ከሚካያ ልጅ ከመታንያ ልጅ፣ ከሸማያ ልጅ፣ ከዮናታን ልጅ፣ ከዘካርያስ ጋራ ነበር።


ባልተቃኘ በገና እንደ ዳዊት ለምትዘፍኑ፣ በሙዚቃ መሣሪያ ለመጫወት ለምትሹ፣


ከይሳኮር የሶገር ልጅ ናትናኤል፤


跟着我们:

广告


广告