Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚክያስ 6:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የክፋት ቤት ሆይ፤ በግፍ የተገኘ ሀብታችሁን፣ በሐሰተኛ መስፈሪያ የሰበሰባችሁትን አስጸያፊ ነገር እረሳዋለሁን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በክፉ ቤት የክፋት መዝገብ፥ አስጸያፊ ሐሰተኛ መስፈሪያ አሁንም አለን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ኃጢአተኛ በቤቱ በክፋት የሰበሰበውን ሀብትና የተረገመውን ሐሰተኛ ሚዛን ልረሳቸው እችላለሁን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በውኑ በኃጢአተኛ ቤት የኃጢአት መዝገብ፥ የተጸየፈውም ውሸተኛ መስፈሪያ ገና አለ ይሆን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በውኑ በኃጢአተኛ ቤት የኃጢአት መዝገብ፥ የተጸየፈውም ውሸተኛ መስፈሪያ ገና አለ ይሆን?

参见章节 复制




ሚክያስ 6:10
21 交叉引用  

ያላግባብ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።


እግዚአብሔር የተጭበረበረ ሚዛንን ይጸየፋል፤ ትክክለኛ መለኪያ ግን ደስ ያሠኘዋል።


ሁለት ዐይነት ሚዛን፣ ሁለት ዐይነት መስፈሪያ፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል።


ሁለት ዐይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ አባይ ሚዛን አይወደድም።


በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣ በንኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው።


“ቅሚያንና ዝርፊያን በምሽጋቸው ውስጥ የሚያከማቹ፣ በጎ ነገር ማድረግን አያውቁም፤” ይላል እግዚአብሔር።


ለአዛጦን ምሽግ፣ ለግብጽም ምሽግ እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤ በውስጧ ያለውን ታላቅ ሁከት፣ በሕዝቧም መካከል ያለውን ግፍ እዩ።”


ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፤ ስሙ! እግዚአብሔር ከተማዪቱን እንዲህ እያለ ይጣራል፤ “በትሩን አስቡ፤ ያዘጋጀውም ማን እንደ ሆነ አስታውሱ።


በዚያ ቀን፣ በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን ሁሉ፣ የአማልክታቸውን ቤት፣ በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትን እቀጣለሁ።”


እኔም፣ “ምንድን ነው?” አልሁት። እርሱም፣ “የኢፍ መስፈሪያ ነው” አለኝ። ቀጥሎም “ይህ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ያለው የሕዝቡ በደል ነው” አለኝ።


እስራኤላውያን ግን ዕርም የሆነውን ነገር ለራሳቸው በመውሰድ በደሉ፤ ይህም ከይሁዳ ነገድ የሆነው አካን የከርሚ ልጅ፣ የዘንበሪ ልጅ፣ የዛራ ልጅ ዕርም ከሆነው ነገር ስለ ወሰደ የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ልጆች ላይ ነደደ።


跟着我们:

广告


广告