Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚክያስ 5:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ጥንቈላችሁን አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አታሟርቱም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የተቀረጹ ምስሎችህንና ሐውልቶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ ለእጅህ ሥራ አትሰግድም፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 መተታችሁን አጠፋለሁ፤ ሟርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ በመካከላችሁ አይገኙም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 መተትንም ከእጅህ አጠፋለሁ፥ ምዋርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆኑልህም፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 መተትንም ከእጅህ አጠፋለሁ፥ ምዋርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆኑልህም፥

参见章节 复制




ሚክያስ 5:12
14 交叉引用  

ጣዖቶች ሁሉ ፈጽሞ ይወድማሉ።


በዚያ ቀን ሰዎች ሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፣ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።


ያዕቆብ የመሠዊያ ድንጋዮችን፣ እንደ ኖራ ድንጋይ ፈጭቶ ሲያደቅቃቸው፣ የአሼራን ዐምድና የዕጣን መሠዊያዎችን፣ ከቦታቸው ነቅሎ ሲጥል፣ በዚያ ጊዜ በደሉ ይሰረይለታል፤ ይህም ኀጢአቱ የመወገዱ ሙሉ ፍሬ ይሆናል።


በቀረው ዕንጨት የጣዖት አምላኩን ይሠራበታል፤ ወድቆ ይሰግድለታል፤ ያመልከዋል፤ ወደ እርሱም እየጸለየ፣ “አንተ አምላኬ ነህ፤ አድነኝ!” ይላል።


ቤቶችሽን ያቃጥላሉ፤ በብዙ ሴቶችም ፊት ቅጣት ያመጡብሻል። ግልሙትናሽን አስተውሻለሁ፤ ከእንግዲህም ለወዳጆችሽ ዋጋ አትከፍዪም።


ንጹሕ ውሃ እረጫችኋለሁ፤ እናንተም ንጹሕ ትሆናላችሁ፤ ከርኩሰታችሁ ሁሉና ከጣዖታቶቻችሁ ሁሉ አነጻችኋለሁ።


“በዚያ ቀን የዳዊትን ቤትና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከኀጢአትና ከርኩሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


ምድራቸውን የምታስለቅቃቸው አሕዛብ፣ መተተኞችን ወይም ሟርተኞችን ያደምጣሉ፤ አንተ ግን ይህን እንድታደርግ አምላክህ እግዚአብሔር አልፈቀደልህም።


ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከርሱም ጋራ በፊቱ ምልክቶችን ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ። በእነዚህ ምልክቶች የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አሳተ። ሁለቱም በሕይወት እንዳሉ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ተጣሉ።


ውሾች፣ አስማተኞች፣ ሴሰኞች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸትን የሚወድዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።


跟着我们:

广告


广告