Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማቴዎስ 27:60 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

60 ለራሱ ከዐለት አስፈልፍሎ ባዘጋጀው መቃብር ውስጥ አኖረው፤ ከዚያም ትልቅ ድንጋይ አንከባልሎ የመቃብሩን በር ዘግቶ ሄደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

60 ከዐለት በወቀረው በአዲሱ መቃብሩ አኖረው፤ በመቃብሩ በር ላይ ትልቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

60 ከአለት ተወቅሮ በተዘጋጀው በራሱ አዲስ መቃብር ውስጥ ቀበረው፤ ከዚህ በኋላ ትልቅ ድንጋይ አንከባሎ የመቃብሩን በር ዘጋና ሄደ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

60 ከዐለት በወቀረው በአዲሱ መቃብርም አኖረው፤ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

60 ከዓለት በወቀረው በአዲሱ መቃብርም አኖረው፥ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ።

参见章节 复制




ማቴዎስ 27:60
12 交叉引用  

‘የምሞትበት ጊዜ ስለ ተቃረበ፣ በከነዓን ምድር ራሴ ቈፍሬ በአዘጋጀሁት መቃብር እንድትቀብረኝ’ ሲል አባቴ አስምሎኛል፤ ስለዚህ ወደዚያ ሄጄ አባቴን ልቅበር፤ ከዚያም እመለሳለሁ።”


‘እዚህ ምን ታደርጋለህ? በዚህ ስፍራ ለራስህ መቃብርን እንድታዘጋጅ፣ በከፍታውም ላይ መቀበሪያህን እንድትወቅር፣ ሬሳህ የሚያርፍበትንም ዐለት እንድትጠርብ ማን ፈቀደልህ?’


በአፉም ሳያታልል፣ ዐመፃም ሳያደርግ፣ አሟሟቱ ከክፉዎች፣ መቃብሩም ከባለጠጎች ጋራ ሆነ።


ዮሴፍም ሥጋውን ወስዶ በንጹሕ የበፍታ ጨርቅ ከፈነው፤


እነርሱም ሄደው መቃብሩን በማኅተም አሽገው ጠባቂ አቆሙበት።


በድንገት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የጌታም መልአክ ከሰማይ ወርዶ ወደ መቃብሩ በመሄድ ድንጋዩን አንከባልሎ በላዩ ላይ ተቀመጠበት፤


ድንጋዩም ከመቃብሩ ደጃፍ ተንከባልሎ አገኙት፤


ኢየሱስ ልቡ ዳግመኛ በሐዘን ተነክቶ ወደ መቃብሩ መጣ፤ መቃብሩም በድንጋይ የተገጠመ ዋሻ ነበር፤


ስለዚህ ድንጋዩን አነሡ። ኢየሱስም ወደ ላይ ተመልክቶ አንዲህ አለ፤ “አባት ሆይ፤ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ፤


ኢየሱስ በተሰቀለበት ቦታም የአትክልት ስፍራ ነበር፤ በአትክልቱም ስፍራ ማንም ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበር።


በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣ በማለዳ ገና ጨለማ ሳለ፣ መግደላዊት ማርያም ወደ መቃብሩ ሄደች፤ ድንጋዩም ከመቃብሩ ተንከባልሎ አየች።


跟着我们:

广告


广告