ማርቆስ 2:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 የፈሪሳውያን ጸሐፍት ከኀጢአተኞችና ከቀረጥ ሰብሳቢዎች ጋራ ሲበላ ባዩት ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱን “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኀጢአተኞች ጋራ ለምን ይበላል?” ሲሉ ጠየቋቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ጸሐፍት ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ “ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድነው?” አሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ የሕግ መምህራን ኢየሱስ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው “ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላውና የሚጠጣው ስለምንድን ነው?” በማለት ደቀ መዛሙርቱን ጠየቁአቸው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ “ከቀራ ጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው?” አሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ፦ ከቀራ ጮችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው? አሉ። 参见章节 |