Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 8:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እየተጓዙ ሳሉም ኢየሱስ እንቅልፍ ወስዶት ተኛ፤ በዚህ ጊዜ በባሕሩ ላይ ማዕበል ተነሣ፤ ውሃውም ጀልባዋን ዘልቆ ስለ ገባ፣ አደጋ አፋፍ ላይ ደረሱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እየሄዱም ሳሉ ኢየሱስ እንቅልፍ ወሰደው። ዓውሎ ነፋስም በሐይቁ ላይ ተነሣ፤ ውኃውም ታንኳይቱን ይሞላ ነበር፤ እነርሱም በአደጋ ላይ ስለ ነበሩ ተጨንቀው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በባሕሩ ላይ እየቀዘፉ ሲሄዱ ሳሉ ኢየሱስ አንቀላፋ፤ በዚያን ጊዜ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ በባሕሩ ላይ ተነሣ፤ ውሃውም በጀልባው ውስጥ መሙላት ስለ ጀመረ አደጋው አስግቶአቸው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ሲሄ​ዱም አን​ቀ​ላፋ፤ በባ​ሕ​ሩም ላይ ዐውሎ ነፋስ መጣ፤ ውኃ​ዉም ታን​ኳ​ቸ​ውን ሞላው፤ እነ​ር​ሱም ተጨ​ነቁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ሲሄዱም አንቀላፋ። ዓውሎ ነፋስም በባሕር ላይ ወረደ፥ ውኃውም ታንኳይቱን ይሞላ ነበርና ይጨነቁ ነበር።

参见章节 复制




ሉቃስ 8:23
13 交叉引用  

እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣ ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣


ጌታ ሆይ፤ ንቃ! ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፤ ለዘላለምም አትጣለን።


“አንቺ የተጨነቅሽ ከተማ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ የተናወጥሽ፣ ያልተጽናናሽም፤ እነሆ፤ በከበሩ ድንጋዮች አስጊጬ እገነባሻለሁ፤ በሰንፔር ድንጋይም እመሠርትሻለሁ።


ሕዝቡ ዙሪያውን እያጨናነቁት የሚያስተምረውን የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰሙ፣ ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ሐይቅ አጠገብ ቆሞ ነበር፤


ከዕለታቱ በአንድ ቀን፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ጀልባ ላይ ወጣ፤ ኢየሱስም፤ “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር” አላቸው፤ ከዚያም ጕዞ ቀጠሉ።


ከአድራሚጢስ ተነሥቶ በእስያ አውራጃ ባሕር ዳርቻ ላይ ወዳሉት ወደቦች በሚሄደው መርከብ ተሳፍረን የባሕር ጕዞ ጀመርን፤ በተሰሎንቄ ይኖር የነበረው የመቄዶንያ ሰው፣ አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋራ ነበረ።


እኛስ ብንሆን ዘወትር ለአደጋ የምንጋለጠው ለምንድን ነው?


በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንምና፤ ነገር ግን እንደ እኛ በማንኛውም ነገር የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁን እንጂ ምንም ኀጢአት አልሠራም።


跟着我们:

广告


广告