Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 8:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “መብራትን አብርቶ በጋን ውስጥ ወይም ከዐልጋ ሥር የሚያስቀምጥ ማንም የለም፤ ይልቁንም ወደ ቤት የሚገቡ ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጠዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “መብራትንም አብርቶ በእንቅብ የሚከድነው ወይም ከአልጋ በታች የሚያኖረው ማንም የለም፤ ይልቅስ የሚገቡት ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያኖረዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “መብራት አብርቶ እንቅብ የሚደፋበት ወይም በአልጋ ሥር የሚያኖረው ማንም የለም፤ ይልቅስ ወደ ቤት የሚገቡ ሁሉ ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያኖረዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 “መብ​ራ​ትን አብ​ርቶ፥ ዕቃም ከድኖ ከአ​ልጋ በታች የሚ​ያ​ኖ​ራት የለም፤ ነገር ግን የሚ​መ​ላ​ለ​ሱት ብር​ሃ​ንን ያዩ ዘንድ በመ​ቅ​ረዝ ላይ ያኖ​ራ​ታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 መብራትንም አብርቶ በዕቃ የሚከድነው ወይም ከአልጋ በታች የሚያኖረው የለም፥ የሚገቡት ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያኖረዋል እንጂ።

参见章节 复制




ሉቃስ 8:16
9 交叉引用  

“መብራት አብርቶ በስውር ቦታ ወይም ከእንቅብ በታች የሚያስቀምጥ ማንም የለም፤ ይልቁን የሚገቡ ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጠዋል።


በመልካም መሬት ላይ የወደቀውም ቃሉን ቅንና በጎ በሆነ ልብ ሰምተው የሚጠብቁ፣ ታግሠውም በመጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።


አንተም ዐይናቸውን ትከፍታለህ፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ትመልሳቸዋለህ፤ እነርሱም የኀጢአትን ይቅርታ ይቀበላሉ፤ በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስት ያገኛሉ።’


በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምስጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።


እነዚህም በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙት ሁለቱ የወይራ ዛፎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው።


跟着我们:

广告


广告