ሉቃስ 5:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ኢየሱስም፣ “ይህን ለማንም አትናገር፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱ ምስክር እንዲሆንም ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ” ሲል አዘዘው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እርሱም ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፤ ነገር ግን፦ “ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ፤” አለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ይህን ነገር ለማንም አትናገር፤ ነገር ግን በቀጥታ ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለሕዝብ ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ለማንም እንዳይናገር ከለከለው፤ “ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አስመርምር፤ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ ነጻህ ሙሴ እንደ አዘዘ መባህን አቅርብ” ብሎ አዘዘው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እርሱም ለማንም እንዳይናገር አዘዘው፥ ነገር ግን፦ ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፥ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ አለው። 参见章节 |