Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 5:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ!” አለው፤ ወዲያውም ለምጹ ጠፋለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ፤” አለው፤ ወዲያውም ለምጹ ለቀቀው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና “ፈቅጃለሁ ንጻ!” አለው። ሰውዬውም ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እጁ​ንም ዘር​ግቶ ዳሰ​ሰ​ውና፥ “እወ​ዳ​ለሁ ንጻ” አለው፤ ያን​ጊ​ዜም ለምጹ ለቀ​ቀው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና፦ እወዳለሁ፥ ንጻ አለው፤ ወዲያውም ለምጹ ለቀቀው።

参见章节 复制




ሉቃስ 5:13
15 交叉引用  

እግዚአብሔርም “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ።


ከዚያም እግዚአብሔር፣ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፤ ደረቁ ምድር ይገለጥ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ።


ኤልሳዕም፣ “ሂድና በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ታጠብ፤ ሥጋህ ይፈወሳል፤ አንተም ትነጻለህ” ብሎ እንዲነግረው መልእክተኛ ላከበት።


ስለዚህ ንዕማን ወረደ፤ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ነገረውም በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ፤ ሥጋውም እንደ ትንሽ ልጅ ሥጋ ሆነ፤ ነጻም።


እርሱ ተናግሯልና ሆኑ፤ አዝዟልና ጸኑም።


ከርኩሰታችሁ ሁሉ አድናችኋለሁ፤ እህሉን እጠራለሁ፤ አበዛዋለሁም፤ ራብንም አላመጣባችሁም።


“እኔ ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ፤ እንዲሁ በፈቃደኛነት እወድዳቸዋለሁ፤ ቍጣዬ ከእነርሱ ተመልሷልና።


ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፤ ንጻ!” አለው። ሰውየውም ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።


እርሱም ወደ ተኛችበት ጠጋ ብሎ በማጐንበስ ትኵሳቱን ገሠጸው፤ ትኵሳቱም ለቀቃትና ወዲያው ተነሥታ አስተናገደቻቸው።


ኢየሱስ ከከተሞች በአንዱ በነበረበት ጊዜ፣ አንድ ለምጽ የወረሰው ሰው በዚያው ከተማ ነበር፤ ይህ ሰው ኢየሱስን ባየው ጊዜ በፊቱ ተደፋና፣ “ጌታ ሆይ፤ ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” ብሎ ለመነው።


ኢየሱስም፣ “ይህን ለማንም አትናገር፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱ ምስክር እንዲሆንም ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን መሥዋዕት አቅርብ” ሲል አዘዘው።


跟着我们:

广告


广告