Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 23:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የኢየሩሳሌም ሴቶች፤ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ እንጂ ለእኔ አታልቅሱ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አለ “እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች፥ ለእኔ አታልቅሱልኝ፤ ይልቁንም ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ መለስ ብሎ፥ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የኢየሩሳሌም ሴቶች፥ ስለ ራሳችሁና ስለ ልጆቻችሁ አልቅሱ እንጂ ስለ እኔ አታልቅሱ!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መለስ ብሎ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ልጆች ሆይ፥ ለራ​ሳ​ች​ሁና ለል​ጆ​ቻ​ችሁ አል​ቅሱ እንጂ ለእ​ኔስ አታ​ል​ቅ​ሱ​ልኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28-29 ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አለ፦ እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች፥ ለእኔስ አታልቅሱልኝ፤ ዳሩ ግን፦ መካኖችና ያልወለዱ ማኅፀኖች ያላጠቡ ጡቶችም ብፁዓን ናቸው የሚሉበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ።

参见章节 复制




ሉቃስ 23:28
10 交叉引用  

እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ እኔ ጥቍር ነኝ፤ ይሁን እንጂ ውብ ነኝ፤ ጥቍረቴ እንደ ቄዳር ድንኳኖች፣ እንደ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት መጋረጃዎችም ነው።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣ ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣ በሚዳቋና በሜዳ ዋሊያ አማፅናችኋለሁ።


ምሰሶዎቹን ከብር፣ መደገፊያውንም ከወርቅ ሠራ፤ መቀመጫውም በሐምራዊ ሐር የተሸፈነ ነው፤ ውስጡም በኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣ ፍቅር የተለበጠ ነው።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣ በሚዳቋና በሜዳ ዋሊያ አማፅናችኋለሁ።


አፉ ራሱ ጣፋጭ ነው፤ ሁለንተናውም ያማረ ነው። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ ውዴ ይህ ነው፤ ባልንጀራዬም እርሱ ነው።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ እማጠናችኋለሁ፤ ውዴን ካገኛችሁት፣ ምን ትሉት መሰላችሁ? በፍቅሩ መታመሜን ንገሩት።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት አማፅናችኋለሁ።


ብዙ ሕዝብና ደረታቸውን እየደቁ የሚያለቅሱለት ሴቶችም ከኋላው ይከተሉት ነበር።


እነሆ፤ ‘መካኖችና ያልወለዱ ማሕፀኖች፣ ያላጠቡ ጡቶችም ብፁዓን ናቸው’ የምትሉበት ጊዜ ይመጣልና።


“እነሆ፤ በደመና ይመጣል፤ የወጉት ሳይቀሩ፣ ዐይን ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከርሱ የተነሣ ዋይ ዋይ ይላሉ።” አዎ! ይህ ሁሉ ይሆናል። አሜን።


跟着我们:

广告


广告