ሉቃስ 16:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 “አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ ‘ልጄ ሆይ፤ አንተ በምድራዊ ሕይወትህ ዘመን መልካም ነገሮችን እንደ ተቀበልህ፣ አልዓዛርም ደግሞ ክፉ ነገሮችን እንደ ተቀበለ አስታውስ፤ አሁን ግን እርሱ እዚህ ሲጽናና፣ አንተ በሥቃይ ላይ ትገኛለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 አብርሃም ግን ‘ልጄ ሆይ! አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም ነገሮችህን እንደተቀበልህ አስብ፤ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል፤ አንተም ትሠቃያለህ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 “አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በምድራዊ ሕይወትህ ዘመን ብዙ መልካም ነገር አግኝተህ እንደ ተደሰትህ አስታውስ፤ አልዓዛር ግን በችግር ላይ ነበር፤ ስለዚህ አሁን እርሱ እዚህ ሲደሰት አንተ ትሠቃያለህ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 አብርሃም ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ተድላና ደስታ እንዳደረግህ፥ አልዓዛርም እንዲሁ ሁልጊዜ በችጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እንዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድላና ደስታ ያደርጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀበላለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 አብርሃም ግን፦ ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም እንደ ተቀበልህ አስብ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል አንተም ትሣቀያለህ። 参见章节 |