Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 12:58 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

58 ከባላጋራህ ጋራ ወደ ዳኛ ፊት ለመቅረብ ስትሄድ፣ ገና በመንገድ ላይ ሳለህ ለመታረቅ ጥረት አድርግ፤ አለዚያ ጐትቶ ወደ ዳኛው ይወስድሃል፤ ዳኛውም ለመኰንኑ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ መኰንኑም ወደ ወህኒ ይጥልሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

58 ከባላጋራህ ጋር ወደ ሹም ብትሄድ፥ ወደ ዳኛ እንዳይጐትትህ ዳኛውም ለሎሌው አሳልፎ እንዳይሰጥህ ሎሌውም በወኅኒ እንዳይጥልህ፥ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ለመታረቅ ትጋ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

58 ባላጋራህ ከሶህ ወደ ፍርድ ቤት በሚወስድህ ጊዜ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ለመስማማት ተጣጣር፤ አለበለዚያ እርሱ ወደ ዳኛ ጐትቶ ይወስድሃል፤ ዳኛውም ለአሳሪው አሳልፎ ይሰጥሃል፤ አሳሪውም ወደ እስር ቤት ያገባሃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

58 ከባ​ለ​ጋ​ራህ ጋር ወደ ሹም በም​ት​ሄ​ድ​በት ጊዜ ወደ ዳኛ እን​ዳ​ይ​ወ​ስ​ድህ በመ​ን​ገድ ሳለህ ታረቅ፤ ዕዳ​ህ​ንም ክፈል፤ ዳኛው ለሎ​ሌው አሳ​ልፎ ይሰ​ጥ​ሃ​ልና። ሎሌ​ውም በወ​ኅኒ ቤት ያስ​ር​ሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

58 ከባላጋራህ ጋር ወደ ሹም ብትሄድ፥ ወደ ዳኛ እንዳይጐትትህ ዳኛውም ለሎሌው አሳልፎ እንዳይሰጥህ ሎሌውም በወኅኒ እንዳይጥልህ፥ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ እንድትታረቅ ትጋ።

参见章节 复制




ሉቃስ 12:58
20 交叉引用  

“ለእግዚአብሔር ተገዛ፤ ከርሱም ጋራ ሰላም ይኑርህ፤ በረከትም ታገኛለህ።


ቅን ሰው ጕዳዩን በርሱ ፊት ያቀርባል፤ እኔም ከፈራጄ ለዘላለም ነጻ እሆናለሁ።


ስለዚህ የምትታመኑት ሁሉ፣ በጭንቅ ጊዜ ወደ አንተ ይጸልይ፤ ኀይለኛ ጐርፍ አካባቢውን ቢያጥለቀልቅም፣ እርሱ አጠገብ አይደርስም።


“እናንተ እግዚአብሔርን የምትረሱ፤ ይህን ልብ በሉ፤ አለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ፤ የሚያድናችሁም የለም።


እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ ቀርቦም ሳለ ጥሩት።


“ነገር ግን ሊታገሠው ፈቃደኛ ስላልነበረ፣ ያለበትን ዕዳ እስኪከፍለው ድረስ ወህኒ ቤት አስገባው።


እርሱ፣ “በተወደደ ጊዜ ሰማሁህ፤ በድነት ቀን ረዳሁህ” ይላልና። እነሆ፤ የተወደደው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳንም ቀን አሁን ነው።


በመንፈስም ሄዶ በወህኒ ቤት ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው።


እነዚህን ነገሮች ከተለየኋችሁም በኋላ ዘወትር ታስቡ ዘንድ እተጋለሁ።


ወዳጆች ሆይ፤ ዐብረን ስለምንካፈለው ድነት ልጽፍላችሁ እጅግ ጓጕቼ ነበር፤ ነገር ግን ለቅዱሳን አንዴና ለመጨረሻ ስለ ተሰጠው እምነት እንድትጋደሉ ለመምከር እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።


ሺሑም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፤


跟着我们:

广告


广告