ሉቃስ 12:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ደግሞም፣ “የሰው ሕይወቱ በሀብቱ ብዛት የተመሠረተ ስላልሆነ ተጠንቀቁ፤ ከስግብግብነትም ሁሉ ራሳችሁንም ጠብቁ” አላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 “የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፤ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ፤” አላቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ቀጥሎ ለሁሉም እንዲህ አላቸው፤ “የሰው ሕይወት በሀብቱ ብዛት አይደለም፤ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ከስስትም ተጠበቁ።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 “ዕወቁ፤ ከቅሚያም ሁሉ ተጠበቁ፤ ሰው የሚድን ገንዘብ በማብዛት አይደለምና” አላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ አላቸው። 参见章节 |