ዘሌዋውያን 7:38 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም38 ይህም፣ በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያን መሥዋዕታቸውን ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡ ባዘዛቸው ቀን በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ የሰጠው ሥርዐት ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)38 ጌታ በሲና ምድረ በዳ ቁርባናቸውን ለጌታ እንዲያቀርቡ ለእስራኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘዘው ይህ ነው።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም38 በዚያም በረሓ በሆነው በሲና ተራራ እስራኤላውያን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ባዘዛቸው በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለሙሴ እነዚህን ትእዛዞች ሰጠው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)38 እግዚአብሔር በሲና ምድረ በዳ ቍርባናቸውን በእግዚአብሔር ፊት ያቀርቡ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘዘው ይህ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)38 እግዚአብሔር በሲና ምድረ በዳ ቁርባናቸውን ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘዘው ይህ ነው። 参见章节 |