ዘሌዋውያን 6:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ማንኛውም ከአሮን ዘር የተወለደ ወንድ ሊበላው ይችላል፤ ለእግዚአብሔር ከሚቀርበው የእሳት ቍርባን ለርሱ የተመደበ የዘላለም ድርሻው ነው፤ የሚነካውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።’ ” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ለጌታ በእሳት ከሚቀረበው ቁርባን ለዘለዓለም ለልጅ ልጃችሁ ድርሻቸው እንዲሆን ከአሮን ልጆች ወንዶቹ ሁሉ ይበሉታል። የሚነካቸው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ትውልዱ ከአሮን ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ለእግዚአብሔር ከቀረበው መባ ለእርሱ የተመደበለትን ፈንታ መብላት ይችላል፤ መባውን የሚነካ ሁሉ በቅድስናው ኀይል ይቀሠፋል።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ከካህናት ወገን ወንድ ሁሉ ይበላዋል፤ በዘመናችሁ ለዘለዓለም ሕግ ነው። ከሚቃጠለው የእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ለእግዚአብሔር ከቀረበ ከእሳት ቍርባን ለዘላለም ለልጅ ልጃችሁ እድል ፈንታቸው እንዲሆን ከአሮን ልጆች ወንዶቹ ሁሉ ይበሉታል። የሚነካቸው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል። 参见章节 |