Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 27:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ከቀንድ ከብቶች፣ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ የሚወጣው ዐሥራት ከእረኛ በትር በታች ከሚያልፉት ዐሥረኛው እንስሳ ይሆናል፤ ይህም ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ከበሬም ሁሉ ከዐሥር አንድ፥ ከእረኛውም በትር በታች ከሚያልፍ በግና ፍየል ሁሉ ከዐሥር አንድ ለጌታ የተቀደሰ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ከቤት እንስሶች ከዐሥር አንዱ እጅ የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፤ እንስሶች በሚቈጠሩበት ጊዜ ከዐሥር አንዱ ለእግዚአብሔር የተለየ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ከበ​ሬም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ፥ ከበ​ግም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ፥ ከእ​ረ​ኛ​ውም በትር በታች ከሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ከበሬም ሁሉ ከአሥር አንድ፥ ከእረኛውም በትር በታች ከሚያልፍ በግና ፍየል ሁሉ ከአሥር አንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 27:32
6 交叉引用  

ይህ ሐውልት አድርጌ ያቆምሁት ድንጋይ፣ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከምትሰጠኝም ሀብት ሁሉ፣ ከዐሥር እጅ አንዱን ለአንተ እሰጣለሁ።”


በተራራማው አገር፣ በምዕራብ ተራሮች ግርጌና በኔጌብ ባሉ ከተሞች በብንያም አገር፣ በይሁዳ ከተሞች እንዲሁም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ መንደሮች መንጎች እንደ ገና በሚቈጥራቸው ሰው እጅ ሥር ያልፋሉ’ ይላል እግዚአብሔር።


ከበትሬ በታች አሳልፋችኋለሁ፤ ከቃል ኪዳኔም ጋራ አጣብቃችኋለሁ።


አንድ ሰው ከዐሥራቱ የትኛውንም መዋጀት ቢፈልግ፣ በዋጋው ላይ አንድ ዐምስተኛ መጨመር አለበት።


ብቻቸውን በዱር ውስጥ፣ በለመለመ መስክ የሚኖሩትን፣ የርስትህ መንጋ የሆኑትን፣ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀድሞው ዘመን፣ በባሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።


“በመገናኛው ድንኳን በሚያገለግሉበት ጊዜ ለሚሠሩት ሥራ ደመወዝ እንዲሆናቸው ከእስራኤል የሚወጣውን ዐሥራት ሁሉ ለሌዋውያን ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።


跟着我们:

广告


广告