ዘሌዋውያን 27:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ዕርሻውን የሚቀድሰው ከኢዮቤልዩ በኋላ ከሆነ ግን፣ ካህኑ ዋጋውን የሚተምነው እስከሚመጣው የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ባሉት ዓመታት ቍጥር ልክ ነው፤ የተተመነውም ዋጋ ይቀነሳል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ነገር ግን እርሻውን ከኢዮቤልዩ ዓመት በኋላ ቢቀድስ፥ ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ እንደ ቀሩት ዓመታት ቊጥር ገንዘቡን ያስላልህስ፤ ከዚያም ከግምትህ ላይ ይቀነሳል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 መሬቱን የሰጠው የኢዮቤልዩ ዓመት ካለፈ ዘግይቶ ከሆነ ግን ካህኑ እስከ ተከታዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ያለውን ቀሪ ጊዜ በመገመት ዋጋው እንዲቀነስ ያድርግ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 እርሻውንም ከኢዮቤልዩ ዓመት በኋላ ቢሳል፥ ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ እንደ ቀሩት ዓመታት ገንዘቡን ይቈጥርለታል፤ ከግምቱም ይጐድላል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 እርሻውንም ከኢዮቤልዩ ዓመት በኋላ ቢቀድስ፥ ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ እንደ ቀሩት ዓመታት ገንዘቡን ይቈጥርለታል፤ ከግምቱም ይጐድላል። 参见章节 |