Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 26:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የዓምናውን እህል እየበላችሁ ከጐተራው ሳያልቅ ለዘንድሮው እህል ደግሞ ቦታ ታስለቅቃላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ለብዙም ጊዜ በጎተራ የተቀመጠውን ቀድሞ የነበረውን እህል ትበላላችሁ፤ ለአዲሱም ቦታ ለማስለቀቅ ቀድሞ በጎተራ የነበረውን ታወጣላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ገና ያለፈውን ሰብል በመብላት ላይ እያላችሁ፥ ለአዲሱ ሰብል ቦታ ማስለቀቅ ይኖርባችኋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ብዙ ጊዜ የተ​ቀ​መ​ጠ​ውን፥ የከ​ረ​መ​ው​ንም እህል ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ አዲ​ሱ​ንም ታስ​ገቡ ዘንድ የከ​ረ​መ​ውን ታወ​ጣ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ብዙ ጊዜ የተቀመጠውንም አሮጌውን እህል ትበላላችሁ፤ ከአዲሱም በፊት አሮጌውን ታወጣላችሁ።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 26:10
5 交叉引用  

“ሕዝቅያስ ሆይ፤ ምልክቱ ይህ ነው፤ “በዚህ ዓመት በገዛ እጁ የበቀለውን፣ በሚመጣው ዓመት ደግሞ የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁ፤ ወይንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።


ዐውድማዎቹ በእህል ይሞላሉ፤ መጥመቂያ ጕድጓዶችም በአዲስ የወይን ጠጅና በዘይት ተሞልተው ያፈስሳሉ።


በስምንተኛው ዓመት በምትዘሩበት ጊዜ፣ የምትበሉት ቀድሞ ከሰበሰባችሁት ሰብል ይሆናል፤ የዘጠነኛውን ዓመት መከር እስክትሰበስቡ ድረስ ከዚሁ እህል ትበላላችሁ።


ይህም ሰው፣ ‘ምርቴን የማከማችበት ስፍራ ስለሌለኝ ምን ላድርግ?’ ብሎ በልቡ ዐሰበ።


ከፋሲካም በኋላ በዚያ ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ማለት ቂጣና የተጠበሰ እሸት በሉ።


跟着我们:

广告


广告