Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘሌዋውያን 25:50 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 እርሱም ራሱን ከሸጠበት ዓመት አንሥቶ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ያለውን ጊዜ ከገዛው ሰው ጋራ በመሆን ይቍጠር፤ ነጻ የሚለቀቅበትም ዋጋ በእነዚያ ዓመታት ለአንድ ቅጥር ሠራተኛ በሚከፈለው መሠረት ይተመናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 ከገዛውም ሰው ጋር ለገዢው ራሱን ከሸጠበት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ያለውን ጊዜ ያሰላል፤ የሽያጩም ብር እንደ ዓመታቱ ቍጥር ይሆናል፤ ከባለቤቱም ጋር የነበረበት ጊዜ ተቀጣሪ አገልጋይ እንደ ነበረበት ጊዜ ተደርጎ ይተመናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 ይህም በሚሆንበት ጊዜ ከገዛው ሰው ጋር ይመካከር፤ ዘመኑንም እርሱ ራሱን ከሸጠበት ዓመት ጀምሮ እስከ ተከታዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቊጠሩት፤ ስለ እርሱም ነጻ መለቀቅ ተገቢውን ዋጋ በእነዚያ ዓመቶች ውስጥ ተቀጥሮ በሚሠራ ሰው ልክ ይተምኑት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 ከገ​ዛ​ውም ሰው ጋር ከገ​ዛ​በት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ ይቍ​ጠር፤ የሽ​ያ​ጩም ብር እንደ ዓመ​ታቱ ቍጥር ይሁን፤ እንደ ምን​ደ​ኛ​ውም ዘመን ከእ​ርሱ ጋር ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 ከገዛውም ሰው ጋር ከገዛበት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቍጠር፤ የሽያጩም ብር እንደ ዓመታቱ ቍጥር ይሁን፤ እንደ ምንደኛውም ዘመን ከእርሱ ጋር ይሁን።

参见章节 复制




ዘሌዋውያን 25:50
10 交叉引用  

እንግዲህ ዘመኑን እንደ ምንደኛ እስኪፈጽም ድረስ፣ ፊትህን ከርሱ መልስ፤ ተወው።


አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የተቀጠረ ሠራተኛ ቀን እንደሚቈጥር፣ የሞዓብ ክብርና የሕዝቧ ብዛት በሦስት ዓመት ውስጥ ይዋረዳል፤ የሚቀረውም ሕዝብ ጥቂትና ደካማ ይሆናል።”


ጌታም እንዲህ አለኝ፤ “በውል የተቀጠረ ሠራተኛ ቀን እንደሚቈጥር፣ የቄዳር ክብር በአንድ ዓመት ውስጥ ያበቃለታል።


ነገር ግን ዋጋውን መመለስ ካልቻለ፣ የሸጠው ርስት እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የገዢው ንብረት ሆኖ ይቈያል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ለባለቤቱ ይመለሳል፤ ሰውየውም ወደ ርስቱ ይመለሳል።


በመካከልህ እንዳለ ቅጥር ሠራተኛ ወይም እንደ እንግዳ አድርገህ ቍጠረው፤ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመትም ይሥራልህ፤


አጎቱ ወይም የአጎቱ ልጅ ወይም ከወገኖቹ ማንኛውም የሥጋ ዘመዱ ይዋጀው፤ ሀብት ካገኘም ራሱን መዋጀት ይችላል።


ብዙ ዓመት የሚቀረው ከሆነም፣ እርሱን ለመግዛት ከተከፈለው ዋጋ ላይ በቀረው ዓመት መጠን ለሚዋጅበት መልስ ይክፈል።


ከዓመት እስከ ዓመት እንደ ቅጥር ሠራተኛ ይኑር፤ አሳዳሪውም በፊትህ በጭካኔ አይግዛው።


አገልጋይህን ዐርነት ማውጣቱ ከባድ መስሎ አይታይህ፤ የስድስት ዓመት አገልግሎቱ፣ አንድ የቅጥር ሠራተኛ የሚሰጠው አገልግሎት ዕጥፍ ነውና። አምላክህ እግዚአብሔር በምታደርገው ነገር ሁሉ ይባርክሃል።


跟着我们:

广告


广告